የራያ ዩኒቨርሲቲ ሰኔት አባላት መስከረም 23 ቀን 2018 ዓ/ም ባካሄዱት መደበኛ ስብሰባ በሶስት የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይተው ውሳኔዎችን አሳልፈዋል። ኣጀንዳዎቹ የድህረ ምረቃ ትምህርት መርሐግብር ለመክፈት ተዘጋጅቶ የቀረበ የዳሰሳ ጥናት ( Needs Assessment) ውጤት መገምገም፣ የአካዳሚክ መርሐግብር ክለሳ ሰነድ ማፅደቅ (Academic Program Review document approval)፣ እንዲሁም የHUAWEI እና CISCO ICT Academy የምስረታ መመሪያዎችን ስለማፅደቅ የሚመለከቱ ሲሆኑ፤ የሰኔት አባላቱ እነዚህ አጀንዳዎች ላይ ተወያይተው ውሳኔዎችን አሳልፈዋል።
በAnimal Genetics and Breeding; Organic Chemistry; Literature; እና Linguistics ትምህርት ክፍሎች የድህረ-ምረቃ ትምህርት መርሐግብሮች ለመክፈት ታስቦ የተደረገው የዳሰሳ ጥናት እና የአካደሚክ መርሐግብር ክለሳ ለማድረግ የተዘጋጀው ሰነድ ቀርበው ሰፊ ውይይት ከተደረገባቸው ቡኃላ እንዲፀድቁ ተደርገዋል። በተጨማሪም በራያ ዩኒቨሪሲቲ የHUAWEI እና CISCO ICT አካዳሚ ለመመስረት የቀረቡ መመሪያዎች በሰኔት አባላቱ ተገምግመው እንዲፀድቁ ሁነዋል። በዚህም መሰረት አካዳሚዎቹ በዪኒቨርሲቲያችን ተከፍተው ስልጠናዎች እንዲሰጡ አቅጣጫ በማስቀመጥ ሰብሰባው ተጠናቅቀዋል።
“”””””””””””””””””””””””””””””””””””””””””
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
ራያ ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
*************”************
የዩኒቨርስቲያችን መርጃዎች ለማግኘት እነዚህን አማራጮች መጠቀም ይችላሉ:-
YouTube: https://www.youtube.com/@RAYAUNIVERSITY
Twitter: https://x.com/RayaUn2008
Website: https://www.rayu.edu.et/
P.O. Box: 92, Maichew

Users Last 7 days : 483
Users Last 30 days : 1775
Total Users : 24574