በዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስር፣ ማህበረሰብ ጉድኝት፣ አስተዳደር እና ልማት ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወር የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም አመላካቾች (KPI) በሚመለከታቸው አካላት ሪፖርት ቀርቦ በዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ዛሬ ሚያዝያ 01/ 2017 በጀት ዓመት በሰኔት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተገመገመ።
የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ስራዎቻችን በቁልፍ ተግባራት የአፈጻጸም አመላካቾች (KPI) ዕቅድ መሰረት በማድረግ እየሰራን መሆኑን ገልፀው ጠንካራ ስራዎቻችን አስቀጥለን ለሚያጋጥሙን ችግሮች ደግሞ ሁነኛ መፍትሄ በማስቀመጥ ዕቅዳችን ማሳካት አለብን ብለዋል።
የፕረዚደንት ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሃይለኪሮስ ከበደ በአሰተዳር እና ልማት ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወር የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም አመላካቾች (KPI) ሪፖርት ዝርዝር ገለፃ አድርገዋል።
ዶ/ር መሐመድአወል የሱፍ በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስር እና ማኅበረሰብ ጉድኝት ዘርፍ የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም አመላካቾች (KPI) የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወር የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም አመላካቾች (KPI) ሪፖርት ለካውንስል አባላት አቅርበዋል።
በተያያዘ ዜና የ2017 በጀት ዓመት የኦዲት ግኝት ሪፖርት በውስጥ ኦዲት ሥራ አስፈፃሚ ቀርቦ በካውንስል አባላቱ እና በሚመለከታቸው አካላት ሀሳብ እና አስተያየት ተሰጥቶበታል።
በመጨረሻም ሁሉም የዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች ተቀናጅቶ በመስራት እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ በማሳካት ተቋሙን የሚመጥን ውጤታማ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅበት ተገልጿል።


*****//*****
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ሚያዝያ 01/2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*****//*****