ለመውጫ ፈተና ከተፈተኑት የራያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል 97.55% አልፈዋል::

በራያ ዩኒቨርሲቲ ከሰኔ 14/2016 ዓ/ም ጀምሮ የተሰጠ የከፍተኛ ትምህርት ለመውጫ ፈተና ከተፈተኑት 286 የራያ ዩኒቨርሲቲ መካከል 279 ተማሪዎች (97.55%) በማለሳለፍ እጅግ በጣም ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል።
ይህ ታላቅ ውጤት እንዲመጣ ትልቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች፣ መምህራን፣ የICT ባለሙያዎች፣ Lab Assistant፣ የኤሌክትሪክ ቴክኒሻኖች፣ ጀነሬተር ኦፕሬተሮች፣ የፀጥታ እና ደህንነት አካላት፣ የማይጨው ዲስትሪክት መብራት ሃይል ሰራተኞች፣ የኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ሪጅን ቅርንጫፍ ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎች ባለሙያዎች ዩኒቨርሲቲው ታላቅ ምስጋናውን ያቀርባል።
መላው የዩኒቨርሲቲያችን አመራሮች፣ ማህበረሰብ እና ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ሰኔ 21/2016 ዐዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!!!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አሥፈፃሚ
*************************************