ራያ ዩኒቨርሲቲ በከባድ ድርቅ ለተጎዱ በቆላ ተምቤን ወረዳ ያቔር እና አከባቢው ማኅበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ እንዲያደርግ በቀረበለት የድጋፍ ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት የዩኒቨርሲቲው ማናጅመንት በወሰነው መሰረት የዩኒቨርሲቲው ልኡካን ቡድን አባላት 50 ኩንታል ፊኖ የምግብ ዱቄት ድጋፍ በመያዝ በድርቁ ለተጎዱ የማኅበረሰብ ክፍሎች ለመርዳት ዛሬ ነሐሴ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ወረዳው ተጉዘዋል።
ዩኒቨርሲቲው ከተመሰረተበት ቁልፍ ዓላማ አንፃር የማኅበረሰቡን ችግር ለመፍታት የተለያዩ የማኅበረሰብ አገልግሎት ስራዎች በመስራት የበኩሉን ማኅበረሰባዊ ግዴታውን እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን ዛሬ ደግሞ በከባድ ድርቅ ለተጎዱ በቆላ ተምቤን ወረዳ #ያቔር ቀበሌ እና አከባቢው የሚኖሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ ለማድረግ ወደ ስፍራው አቅንቷል።
የልኡካን ቡድኑ አባላት በቦታው ተገኝተው የወረዳው አመራርና የሚመለከታቸው አካለት በተገኙበት ለተጎጂው ማህበረሰብ ድጋፉን የሚያበረክት ሲሆን ዩኒቨርሲቲው በቀጣይም የህዝብ አለኝታነቱን ለማረጋገጥ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል።
*****//*****
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ነሐሴ 01 ቀን 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
*****//*****


