(ራያ ዩኒቨርስቲ፤ ህዳር 12/2018 ዓ/ም)
ለራያ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ሥራ አስፈፃዎችና ቡድን መሪዎች በተቀናጀ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ስርዓት Integrated Financial Management Information System (IFMIS) አተገባበር ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከገንዘብ ሚኒስቴር በመጡ ባለሙያዎች ተሰጥቷል።
በመድረኩ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የራያ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ልዩ ረዳት መ/ር ትኩየ ደርቤ ሲሆኑ በንግግራቸው በተቋማችን በኢፍሚስ ዝርጋታ በቅርቡ እንደሚጀምር ፣ ከጥር 01/2018 ጀምሮ ወደ ሲስተም እንደሚገባ እና ሁሉም የፋይናንስና የንብረት አስተዳደር ስራዎችና ምዝገባዎች በኢፍሚስ ብቻ እንደሚሆኑ ገልፀዋል፡፡
ከገንዘብ እና ኢኮነሚ ሚኒስቴር በኩል አሬንቴሽኑን የሰጡት የገንዘብ ሚኒስቴር ባለሙያ የሆኑት አቶ ዮሴፍ አገኘሁ የተቀናጀ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር መረጃ ስርዓት (IFMIS) አሁን የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነና ሁሉም የፌደራል ተቋማት ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ ቁርጠኛ መሆን እንደሚገባቸውና ራያ ዩኒቨርስቲ ከጥር 1/2018 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ሲስተም መግባት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ባለሙያው አክለውም ለስድስት ወራት በዩኒቨርሲቲው በሚኖራቸው ቆይታዎች ለሰራተኞች የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎችን በመስጠትና ባለሙያዎችን በማብቃት ላይ እንደሚሰሩም ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ልዩ ረዳት መ/ር ትኩየ ደርቤ ኢፍሚስ ዘመኑ የደረሰበት ቴክኖሎጅ ሥራዎችን በፍጥነት በማከናወን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ፣ በተቋም ከወረቀት ንክኪ ነፃ የሆነ አሰራር እንዲኖር፣ የጊዜና የሀብት ብክነትን ለመቀነስ እና በዘርፉ ግልፅነት ባለው መልኩ ሥራዎችን ለመሥራት የሚያስችል መሆኑን በመጠቆም የሚመለከታቸው አካላት ኦሬንቴሽኑን በተገቢው በመከታተልና በመረዳት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተግባር እንዲገቡ አሳስቧል። በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተግባር እንዲገቡ አሳስቧል።
*********************************
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
ራያ ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
****************
የዩኒቨርሲቲያችን መረጃዎች ለማግኘት እነዚህን አማራጮች መጠቀም ይችላሉ:-
Facebook: https://www.facebook.com/RayaUniversityofficial
YouTube: https://www.youtube.com/@RAYAUNIVERSITY

Users Last 7 days : 485
Users Last 30 days : 1878
Total Users : 24823