በዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚደንት ፕሮፌስር ታደሰ ደጀኔ እና የትግራይ ግብርና ቢሮ ኃላፊ እያሱ ኣብርሃ (ዶ/ር) የተመራ የመስክ ጉብኝት ተክሄደዋል። ግቡኝቱ በራያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር፣ ማሕበረሰብ አገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት የተሰሩ የተለያዩ የግብርና የምርምር ውጤቶችን ለአከባቢው ማሕበረሰብ ለማጋራት ያለመ ሲሆን ከሁሉም የዞኑ ወረዳዎች የተውጣጡ አርሶ አደሮችና የግብርና ባለሙያዎች ተሳትፎውበታል።

የራያ ዩኒቨርስቲ የግብርና ኮሌጅ መምህራን፣ ተማራማሪዎች እና ባለሙያዎች በአዝርእት ብዜት፣ የመኖና እና እንስሳት የማደለብ ስራዎች እንዲሁም የንብ እርባታ ላይ እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ተገኝተው ሙያዊ ገለፃና ማብራርያ የሰጡ ሲሆኑ ጎብኝዎቹ አርሶ አድሮችና የዞኑ የግብርናና ገጠር ልማት ባለሙያዎችም በመስክ ጉብኝቱ በጣም እንደተደሰቱ ገልፀዋል።
በመርኃግብሩ ማገባዳጃ የአደራሽ ላይ ውይይት እና የምክክር መድረክ የነበረ ሲሆን ጎብኙዎች የነበሩዋቸው ኃሳብ አስተያየቶች አቅርበው በዩኒቨርስቲያችን ፕሬዚደንት ፕሮፌስር ታደሰ ደጀነ፣ የትግራይ ግብርና ቢሮኃላፊው እያሱ አብርሃ (ዶ/ር) እንዲሁም በዩኒቨርሲቲያችን የምርምር፣ ማሕበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተ/ምክትል ፕሬዚደንት መሓሪ ሃይለ (ዶ/ር) ማብራርያ ተሰጥታቸዋል።
======================================
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
ራያ ዩኒቨርሲቲ
‎የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
‎**********
‎ የዩኒቨርሲቲያችን መረጃዎች ለማግኘት እነዚህን አማራጮች መጠቀም ይችላሉ:-
‎P.O. Box: 92, Maichew