ጥቅምት 7፣ 2018 ዓ/ም (ራዩ)፤
የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ከሶስቱም የዩኒቨርቲው ምክትል ፕሬዚደንቶች ጋር የቁልፍ አፈጻጸም አመልካቾች (KPI) የኮንትራት ውል ትላንት ጥቅምት 6፣ 2018 ዓ/ም ተፈራርመዋል። የፌርማ ስነስርዓቱን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ የውሉን አስፈላጊነት አስመልክተው ባሰሙት ንግግር ይህ የአፈፃፀም ውል የዩኒቨርሲቲው አንኳር አንኳር ተልእኮዎች ቆጥሮ በመስጠትና በመረከብ የጥራት ስታንዳርድ በጠበቀ ሁኔታ እንዲከናወኑ የሚያግዝ ውል መሆኑን አብራርተዋል። አክለውም እያንዳንድዱ የዩኒቨርሲቲው አባል በዩኒቨርስቲው ተለይተው የተቀመጡ የአፈፃፀም አመላካቾችና አንኳር ተልእኮዎች በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን የበኩሉን ሚና መጫወት እንዳለበት አሳስበዋል።
የየድርሻቸው የአፈፃፀም ኮንትራት ውል የተፈራረሙት የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት ነጋ ዓፈራ (ዶ/ር)፣ የአስተዳደርና ልማት ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት ክብሮም ካሕሱ (ዶ/ር)፣ እንዲሁም የምርምር፣ ማሕብረሰብ ጉድኝንት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተ/ምክትል ፕሬዚዳንት መሓሪ ሃይለ (ዶ/ር) በበኩላቸው ዘመኑ የውድድር ስለሆነ እንደ ዩኒቨርሲቲ በመማር ማስተማር፣ ምርምርና ማሕብረሰብ አገልግሎት፣ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ትስስሮችና አለም አቀፍ ግንኝነቶች የሚጠበቁበት እያንዳንዱ የአፈፃፀም መለክያዎች ካባለፉት አመታት በተለየ የአፈፃፀም ደረጃ ማከናወን አለበት ብለዋል። አክለውም ሁሉም በየደረጃው ያሉ አመራሮችና የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ይሄንን የተጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት ደከመን ስለቸን ሳይሉ መስራት እንዳለባቸው በአፅንኦት አሳስበዋል።
==========================
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
ራያ ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
**********
የዩኒቨርሲቲያችን መረጃዎች ለማግኘት እነዚህን አማራጮች መጠቀም ይችላሉ:-
YouTube: https://www.youtube.com/@RAYAUNIVERSITY
Twitter: https://x.com/RayaUn2008
Website: https://www.rayu.edu.et/
P.O. Box: 92, Maichew

Users Last 7 days : 495
Users Last 30 days : 1787
Total Users : 24586