ራያ ዩኒቨሪሲቲ ከECDC የኮምፕዩተሮች ድጋፍ ተበረከተለት! ====================================

(ራያ ዩኒቨርሲቲ፤ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ/ም)
ራያ ዩኒቨርሲቲ Ethiopian Community Development Council (ECDC) Inc, ከተሰኘ እ.አ.አ በ1983 በዶ/ር ፀሃየ ተፈራ ከተመሰረተው የበጎ-አድራጎት ድርጅት የኮምፕዩተሮች ድጋፍ ተበረከተለት። ECDC ዛሬ መስከረም 26 ቀን፣ 2018 ዓ/ም የራያ ዩኒቨሪሲቲ የጋርዮሽ ሳይንስ መርኃግብር (Science Shared Program) ለማጠናከር አልሞ በቁጥር 30 የሚሆኑ የApple Laptop ኮምፕዩተሮች ለዩኒቨርስቲያችን ድጋፍ አድርጓል። የድጋፉ ርክክብ የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ፤ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ነጋ ዓፈራ (ዶ/ር)፣ የScience Shared መርኃግብር ዳይሬክተር በርሀ አከለ (ረ/ፕ) እና በየደረጃው ያሉ ሌሎች የመርኃግብሩ አመራሮች፤ እንዲሁም መምህራኖች እና ተማሪዎች በተገኙበት ተካሂደዋል።
የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ድጋፉን ላበረከተ ECDC አመስግነው፤ የScience Shared ተማሪዎች ካለ ምንም የቁሳቁስ ድጋፍ የዪኒቨርሲቲያችን ስም በከፍተኛ ደረጃ እያስጠሩ ያሉ በመሆናቸው ባለ-ተስፋ መሆናቸውን ገልፀው፣ በቀጣይነት የመርኃ ግብሩ ተደራሽነት ለማስፋት ከብዙ አካላት ጋር መተባበር እንደሚገባ በአፅንኦት ተናግረዋል። አክለውም ይህ የScience Shared Program ጅምሩ ትንሽ ቢመስልም ለማህበረሰቡ እያበረከተው ያለ ሚና ለማይጨው ከተማ ወይም ለደቡባዊ ዞን ብቻ ሳይሆን፤ ለመላው ትግራይ እንዲሁም ለሀገር የሚተርፍ መሆኑንና፤ ዩኒቨርሲቲው እንዲሁም ሁሉም ባለድርሻ አካላት አበክረው ሊሰሩበት የሚገባ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
የዩኒቨርሲቲያችን የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ነጋ ዓፈራ (ዶ/ር) በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲያችን የScience Shared Program ስጀምር የተሟላ የቁሳቁስ አቅርቦት ኑሮት ሳይሆን የማህበረሰቡና የተማሪዎቹ የትምህርት ፍላጎት ብቻ ይዞ፣ ቁሳቁሶቹ በሂደት እንደሚሟሉ በማመን እንደነበር አውስተው ECDC የዚህ ተነሳሽነት አጋዥ ሁኖ ድጋፍ ማድረጉን ልባዊ ምስጋና ይገበዋል ብለዋል።
ከECDC የተገኙት ኮምፕዩተሮች የተረከቡት የራያ ዩኒቨርሲቲ የጋርዮሽ ሳይንስ መርኃግብር (Science Shared Program) ዳይሬክተር የሆኑት በርሀ ኣከለ (ረ/ፕ) ደግሞ ድጋፉ ላበረከተ ECDC፤ እንዲሁም በሂደቱ ብዙ አስተዋጽኦ ላደረጉ የዩኒቨርሲቲያችን ባልደረባ ህንፃ ገብረገርግስ (ረ/ፕ) እና ሌሎች አመራሮች አመስግነው፤ ድጋፉ ቀጣይነት እንደሚኖረው አልጠራጠርም ብለዋል። አክለውም ይህ ድጋፍ ምንም በሌለበት የሚያስደንቅ ውጤት ለምያስመዘግቡ የመርኃግብሩ ተማሪዎች ይበልጥ ጠንክረው እንዲማሩና የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ የሚያግዛቸው እንደሆነ ገልፀዋል።
በተጨማሪም የScience Shared መምህራኖች እና ተማሪዎች በድጋፉ ዙርያ ሀሳባቸው የሰጡ ሲሆን ECDCን አመስግነው፣ የተሻለ ውጤት በማምጣት ለራያ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ድጋፍ ለሚያደርጉላቸው አጋር አካላት የሚያኮራ ተግባር ለመፈፀም እንደተዘጋጁ ቃል ገብተዋል። አክለውም ይሄን መሰል ድጋፎች ተጠናክሮው እንዲቀጥሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
==================================
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
ራያ ዩኒቨርሲቲ
‎የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
‎***************************
‎የዩኒቨርሲቲያችን መረጃዎች ለማግኘት እነዚህን አማራጮች መጠቀም ይችላሉ:-
‎P.O. Box: 92, Maichew