‎ራያ ዩኒቨርሲቲ ለፍሬምናጦስ የአረጋውያን፣ ህፃናት እና አእምሮ ህሙማን እንክብካቤ ማእከል የቁሳቁስ ድጋፍ አበረከተ

‎ራያ ዩኒቨርሲቲ ለፍሬምናጦስ የአረጋውያን፣ ህፃናት እና አእምሮ ህሙማን እንክብካቤ ማእከል ዛሬ ነሐሴ 06 ቀን 2017 ዓ.ም ከ1.2 ሚልዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል።
‎የድጋፍ ቁሳቁሶቹ በዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ በኩል የተበረከቱ ሲሆን በዋናነት ለኩሽና፣ ለመኝታ፣ ለምግብና እና ሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ ናቸው።
‎በፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ የተመራው የዩኒቨርሲቲው ልኡክ ቡድን አባላት በማእከሉ አረጋውያኑ፣ ህፃናቱ እና አእምሮ ሕሙማኑ ያሉበት ሁኔታ እንዲሁም በማእክሉ እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ ስራዎች ጎብኝተዋል።
‎በመጨረሻም የእንብካቤ ማእከሉ አስተዳዳሪ አባ ገብረመድህን ለዩኒቨርሲቲው ልኡክ ቡድኑ አባላት የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልእክት በማስተላለፍ በማእከሉ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ዝርዝር ገለጻ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
‎*****//*****
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ነሐሴ 06 ቀን 2017 ዓ.ም
‎ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
‎የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
‎*****//*****