በማይጨው ከተማ ባለው ከፍትኛ የመኖርያ ቤት ችግር የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን መደበኛ ስራቸውን እንዳይሰሩ ትልቅ ተፅእኖ እየፈጠረ እና የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ በመቆየቱ የራያ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ አመራሩ የመምህራን መኖሪያ ቤት ችግር በጣም አንገብጋቢ እና የቅድሚያ ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶ በ2017 ዓ/ም እንዲሰራ በመወሰኑ የግንባታ ስራውን ተጀምሯል።
በዩኒቨርሲቲያችን የተጀመረውን የመምህራን መኖሪያ ቤት ግንባታ ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ፣ የአሰተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ክብሮም ካሕሱ፣ ኮሌጅ ዲኖች፣ የግንባታ ጽ/ቤት ባለሙያዎች፣ አማካሪ እና ኮንትራክተሮች ዛሬ ግንቦት 12/ 2017 ዓ.ም የጎበኙት ሲሆን የግንባታ ሂደቱ በጥራት፣ በፍጥነት እና በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የክትትልና ቁጥጥር ስራ እንደሚደረግ ተገልጿል።








********************//********************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ግንቦት 12/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት
********************//*************************