ራያ ዩኒቨርሰቲ ‎ የንብረት አስተዳደር ስራውን ለማዘመን የተለያዩ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ “የቋሚ ንብረቶች እርጅና ቅነሳ ጽንሰ ሀሳብ” በተለያየ ደረጃ ለሚገኙ የዩኒቨርሲቲው የንብረት አስተዳደር ባለሙያዎች የዓቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

ይህ የተገለጸው ‎በራያ ዩኒቨርሲቲ የንብረት አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት አዘጋጅነት በንብረት አያያዝ፣ አጠቃቀም፣ አወጋገድ እና የቋሚ ንብረቶች እርጅና ቅነሳ ጽንሰ ሀሳብ እንዲሁም በንብረት አስተዳደር ዙርያ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች እና የመፍትሔ ስትራቴጂዎች ላይ ያተኮረ በተለያየ ደረጃ ለሚገኙ የዩኒቨርሲቲው የንብረት አስተዳደር ባለሙያዎች አና ለሚመለከታቸው አካላት ዛሬ ግንቦት 09 ቀን 2017 ዓ.ም በመኾኒ ከተማ የዓቅም ግንባታ ስልጠና በተሰጠበት ወቅት ነው፡፡
‎ሥልጠናው፤ ዩኒቨርሲቲው የንብረት አስተዳደር ስርዓቱን ለማዘመን እያከናወናቸው ላሉ ፈርጀ ብዙ ስራዎች ለመደገፍ እና የባለሙያዎቹ ዓቅም በማጠናከር በዘርፉ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ ያለመ ነው፡፡
‎የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ተወካይ አቶ ሞገስ ገብረሂወት ስልጠናውን አስመልክተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ በንብረት አስተዳደር ዘርፍ እየተሰራ ያለው ስራ ለማጠናከር እና አገልግሎቱን ለማዘመን ሁሉም ባለሙያ አንድ ጊዜ ባገኘው ዕውቀት ብቻ ብቁ ስለማይሆን እንደዚህ ዓይነት አጫጭር ስልጠናዎችን በተከታታይ በመስጠት ባለሙያውን ማነቃቃት እና ማዘመን አስፈላጊ ስለሆነ በሚሰጣችሁ ስልጠና መነሻ በማድረግ ራሳችሁን ማብቃት ይጠበቅባችኃል ብለዋል።
‎ስልጠናውን የሰጡት የዩኒቨርሲቲው የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን መምህር ሃፍቱ አረፈ (ዶ/ር) የመንግስት ንብረት አስተዳደር መመሪያ 649/2011 መሰረት በማድረግ የቋሚ ንብረቶች የእርጅና ቅነሳ መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች፣ መርህ፣ ዓይነት፣ ሂደት፣ ሪፖርት አቀራረብ እንዲሁም በዘርፉ ላይ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
‎በስልጠናው ከተሳታፊዎች ጋር በተደረገ ውይይት የንብረት አስተዳደር መመሪያዎችን ጠንቅቆ በመረዳት በዩኒቨርሲቲው ወጥ የሆነ አሰራር እንዲኖር ለማድረግ እና የሚታዩ የአሰራር ክፍተቶችን ለመቅረፍ በዘርፉ ለውጥ በማምጣት የዩኒቨርሲቲው ውጤታማነት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል፡፡
‎በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው የንብረት አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አልማዝ ሃይለ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር፤ መንግስት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የንብረት አስተዳደር ስርዓት ለማዘመን ዘርፈ ብዙ ሪፎርሞችን እያከናወነ ይገኛል በማለት በዩኒቨርሲቲያችንም በዘርፉ የባለሙያዎች እጥረት እና የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢኖርም አስፈላጊውን ግብዐት በማሟላት እና በተሰጠው ስልጠና በመነቃቃት የንብረት አስተዳደር ስርዓቱ ለማዘመን ውጤታማ ስራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
‎*****‎*****‎*****‎*****//*****‎*****‎*****
‎ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ግንቦት 09 ቀን 2017 ዓ.ም
‎ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
‎የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
‎*****‎*****‎*****‎*****//*****‎*****‎*****