‎በተለያየ ደረጃ ለሚገኙ የዩኒቨርሲቲው ባለሙያዎች የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ግምገማና ሪፖርት አቀራረብ ሥልጠና ተሰጠ

‎በራያ ዩኒቨርሲቲ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት አዘጋጅነት ቁልፍ የውጤት አመላካቾች መሰረት በማድረግ በተለያየ ደረጃ ለሚገኙ የዩኒቨርሲቲው ባለሙያዎች የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ግምገማና ሪፖርት አቀራረብ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
‎የሥልጠናው ዓላማ በዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትል፣ ግምገማና ሪፖርት አቀራረብ ዙሪያ የሚስተዋለውን ክፍተትና የአቅም ውስንነት ችግሮችን በመቅረፍ የታዩትን ክፍተቶች ለመሙላት ነው፡፡
‎የዩኒቨርሲቲው የስትራቴጅክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ መምህር ጋሻው ተፈሪ በቁልፍ የውጤት አመላካቾች ዕቅድ ዝግጅት፣ ሪፖርት አቀራረብ፣ ክትትል፣ ግምገማና ግብረ መልስ አሰጣጥ ጽንሰ ሀሳብ ምንነት፣ ባህርያት፣ ዓይነቶች፣ ሂደቶች፣ እና በዘርፉ የሚስተዋሉ ክፍተቶች ሰፋ ያለ ሙያዊ ማብራሪያ በመስጠት በተለይ በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደረጃ የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎች እየተካሄዱ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ የዩኒቨርሲቲው ራዕይ እና ተልዕኮ ባገናዘበ መልኩ ዕቅድ ማቀድ፣ መተግበር፣ ክትትል ማድረግና ተገቢዉን የሪፖርት ማጠናቀሪያ ፎርማት በመጠቀም የተሠሩ ሥራዎችን ሪፖርት ማድረግ የሚጠበቅ ተግባር በመሆኑ ይህንኑ ተግባር ማከናወን እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
‎ከተሳታፊዎች ጋር በተደረገ ውይይት ቁልፍ የውጤት አመላካቾች ዕቅድ መሰረት በማድረግ ሁሉም ባለሙያ በየደረጃው ቁልፍ የውጤት አመላካቾች እቅድ በአግባቡ ተገንዝቦ በመፈጸም፣ በተዘረጋው የክትትል እና የድጋፍ ስርዓት መሰረት እውነተኛ፣ ተአማኒ እና የተሰነደ ሪፖርት በማቅረብ የዩኒቨርሲቲውን ራእይ እና ተልእኮ ማሳካት እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡
‎በመጨረሻም ተሳታፊዎች በቀረበው ገለጻ ላይ ያላቸውን ጥያቄዎችና አስተያየቶች እንዲሁም ሊሟሉ ይገባሉ ያሏቸውን ግብዐቶች በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት በበኩላቸው ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
‎*****‎*****‎*****‎*****//*****‎*****‎*****
‎ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ግንቦት 08/ 2017 ዓ.ም
‎ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
‎የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
‎*****‎*****‎*****‎//*****‎*****‎*****‎*****‎*****