የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ጽ/ቤት ይፋ ባደረገው መርሃ ግብር መሰረት የ2017 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና ከሰኔ23እስከሐምሌ8/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል።
በመርሃ ግብሩ መሰረት ወደ ዩኒቨርሲቲያችን የተመደቡ በወረቀትየሚፈተኑየተፈጥሮሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ21 እስከ 22/2017 ዓ/ም እንዲሁም የማህበራዊሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 29 እስከ 30/2017 ዓ/ም ይገባሉ።
እንደ አገልግሎት ጽ/ቤቱ ይፋዊ መርሃ ግብር፤ በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተፈታኞች ከመኖሪያ ቤታቸው በየቀኑ እየተመላለሱ በተመደቡበት መፈተኛ ማዕከል የሚፈተኑ ሲሆን አንደኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የበይነ መረብ ተፈታኞች ከሰኔ23-25/2017 ዓ.ም እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ ከሐምሌ01-03/2017 ዓ.ም እንደሚፈተኑ ተመላክቷል።
ሁለተኛ ዙር የበይነመረብተፈጥሮሳይንስ ፈተና ሰኔ26፣27እና30/2017 ዓ.ም እንዲሁም የማህበራዊሳይንስ ፈተና ሐምሌ4፣7እና8/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል።
የፈተናው ይዘት በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያተኮረ በመሆኑ እያንዳንዱ ተፈታኝ በትምህርት ቤቱ የተማረበትን የተማሪመጽሐፍ መሠረት አድርጎ ተገቢ የሆኑ አጋዥ መጽሐፍትን ለበለጠ እውቀትና መረዳት በመጠቀም እንዲዘጋጅ አገልግሎቱ ጥሪውን አስተላልፏል።
በዚህ አጋጣሚ ራያ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን የወረቀት እና የበይነ መረብ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ተቀብሎ ለመፈተን አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹን አጠናቅቆ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።
በመጨረሻም በፈተና ወቅት ለፈተና ስርቆትና ኩረጃ የሚውሉ ማንኛውንም ቁሳቁሶች መጠቀም የተከለከለ ነው ተብሏል።
*****************//*********************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ግንቦት 02 ቀን 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማህበሰባዊ ለውጥ
የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት
*********************//*********************