‎የ2017 ዓ.ም የዓቅም ማሻሻያ መርሐ ግብር (Remedial Program) ተማሪዎች በበይነ መረብ የሞዴል ፈተና እየተሰጠ ነው

‎ራያ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡለትን በወረቀት እና በበይነ መረብ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ተቀብሎ ለመፈተን አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹን አጠናቅቆ በመጠባበቅ ላይ የሚገኝ ሲሆን የዚህም ማሳያ በዩኒቨርሲቲው የ2017 ዓ.ም የዓቅም ማሻሻያ መርሐ ግብር (Remedial Program) የማህበራዊ እና ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች (12ኛ ክፍል ተማሪዎች) ከዛሬ ግንቦት 04/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በበይነ መረብ ሞዴል ፈተና እየወሰዱ ይገኛሉ።
‎‎የፈተና ሂደቱ የዩኒቨርሲቲው የአካ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/አገልግሎት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ነጋ ዓፈራ እንዲሁም የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ክብሮም ካሕሱ ጎብኝተውታል።
‎********************//*************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ግንቦት 04 ቀን 2017 ዓ.ም
‎ዕውቀት ለማህበሰባዊ ለውጥ
‎የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት
‎*************************//*************************