ዩኒቨርሲቲው የ2017 ዓ/ም የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተማሪዎቹ ልዩ የምሳ ግብዣ መርሃ ግብር አዘጋጀ

ዩኒቨርሲቲው የ2017 ዓ/ም የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ለተማሪዎቹ ልዩ የምሳ ግብዣ መርሃ ግብር ያዘጋጀ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ የሃይማኖች መሪዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች እና የማኅበረሰብ ተወካዮች በጋራ በመሆን የ2017 ዓ.ም የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓልን ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጋር በድምቀት አክብረዋል፡፡
ለተማሪዎቹ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስተላለፉት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ነጋ ዓፈራ፤ በዓሉ የሰላም፣ የአብሮነት፣ የፍቅር፣ የጤና፣ የመተባበር፣ የይቅርታ እና የመደጋገፍ እሴቶቻችን የሚያደምቅ በዓል ነው ብለዋል።
የተማሪዎች አገልግሎት ዲን መምህር ረዳኢ ስብሃቱ በመርሃ ግብሩ እንደተናገሩት በዓሉ የሰላም፣ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት፣ የአብሮነት፣ የፍቅር እና የይቅርታ እንዲሆን ለተማሪዎቹ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።
የማይጨው ወረዳ ቤተ ክህነተ ሊቀ ካህናተ መልአክሳህል ሃይለመለኮት ፀጋይ በመርሃ ግብሩ፤ የትንሳኤ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ሲል ለሰው ልጅ ያለውን ፍቅሩን ያስተማረበት፣ ከበደልና በቀል ይልቅ ይቅርታና ምህረትን እንድንማር አምነንም እንድንኖርበት የእምነት ምሶሶ የተተከለበት ታላቅ በዓል ነው ብለዋል።
የማይጨው መስጂድ ኢማም ሸኽ መሐመድ አሚን በበኩላቸው ይህን ታላቅ ሀይማኖታዊ በዓል ሲከበር የመተጋገዝ፣ የመረዳዳት፣ የአብሮነት እና የመከባበር መንፈስ የሚያጎለብት መሆን አለበት ብለዋል።
የቃለ ህይወት ቤተ ክርስቲያንን በመወከል ለተማሪዎቹ መልእክት ያስተላለፉ መምህር አድነው ወልደገብርኤል፤ የትንሳኤ በዓል በክርስትና አምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበር እና ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያለውን ጥልቅ ፍቅር የገለጠበት ድንቅና ታላቅ በዓል በመሆኑ በዓሉ በመከባበር ልናከብረው ይገባል ብለዋል፡፡
የትንሣኤ በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የመቻቻል፣ የመደጋገፍ፣ የመተባበር፣ የመተሳሰብና የአንድነት የምናፀባርቅበት በዓል ነው ያሉት የማይጨው አጥቢያ ወንጌላውያን ህብረት ሰብሳቢ አቶ ገብረመድህን ፍቃዱ ናቸው።
የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በበኩላቸው በተዘጋጀላቸው ልዩ የበዓል መርኃ ግብር መደሰታቸውን ገልፀዋል።
ዩኒቨርሲቲው በድጋሜ መልካም የፋሲካ በዓል እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልፃል!
*****//*********************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ሚያዝያ 12/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*****//*********************************