ራያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን የመጀመርያ እና ሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች ነገ ማክሰኞ ሰኔ 25/2016 ዓ/ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድና ቀጠናዎች ትስስር ሚኒስቴር ዲኤታ እና የራያ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ካሳሁን ጎፌን ጨምሮ ሌሎች የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ አመራሮች እና ማህበረሰብ በተገኙበት አዲስ በተመረቀው አዳራሽ በደማቅ ስነ ስርዓት ያስመርቃል።
ዩኒቨርሲቲው ለተመራቂ ተማሪዎች እና የተመራቂ ተማሪዎች ቤተሰብ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል።
*****************************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ሰኔ 24/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*****************************************

Users Last 7 days : 353
Users Last 30 days : 1571
Total Users : 23030