ማኅበራዊ ትስስራችን ለአብሮነታችን!” በሚል መሪ ቃል የጎንደር ቃል ኪዳን ቤተሰብ ሀገር አቀፍ የልምድ ልውውጥ መድረክ ዛሬ ሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።
መድረኩ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚኒስቴር እና ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ እና የዩኒቨርሲቲው የሀገር ግንባታ ፎካል ፐርሰን ዶ/ር ገሰሰ ንጉስን ጨምሮሁሉንም የዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በመድረኩ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕረዝደንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን፣ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሐመድ እንድሪስ፣ በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሄራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኔስቴር ዴኤታ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ወ/ሮ ደብሬ የኃላ የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልእክት እና ስለ ልምድ ልውውጡ ሀሳብ ሲሰጡ የቃልኪዳን ቤተሰብ ፋይዳ፣ ስለአብሮነት፣ ፍቅር እና ማኀበረሰብን በማስተሳሰር ረገድ ስላለው ጠቀሜታና ለሰላም ስላለው አስተዋፅኦ በዝርዝር ተናግረዋል።
ሀገር አቀፍ የልምድ ልውውጥ መድረኩ በተለያዩ መርሐ ግብሮች የሚቀጥል ይሆናል።












********************//**************
ሀምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
********************//*************