ዩኒቨርሲቲው የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እና ለማስፋፋት በትኩረት እየሰራ ነው

በራያ ዩኒቨርሲቲ የፍራፍሬ ጠብታ መስኖ (Drip Irrigation) ቴክኖሎጂ 4 ሄክታር፣ አዲስ የጠብታ መስኖ (Drip Irrigation) ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ 3 ሄክታር፣ ስፕሪንክለር (Sprinkler) ቴክኖሎጂ 3 ሄክታር በጠቅላላ ከ10 ሄክታር በላይ የእርሻ ማሳ ማልማት የሚያስችል የጠብታ መስኖ (Drip Irrigation) ቴክኖሎጂ በብሩህ ተስፋ የመስኖ ውሃ ቴክኖሎጂ ፋብሪካ ተሰርቶ ሚያዝያ 03/ 2017 ዓ/ም የርክክብ ስነ ስርዓት ተካሄደ።
በርክክብ ሂደቱ የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ታደሰ ደጀኔ (ፕሮፌሰር)፤ ዩኒቨርሲቲው የግብርና ዘርፍ ለማዘመን ለማስፋፋት የተለያዩ የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች በመስራት የዘር ብዜት እና የውስጥ ገቢ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
የግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ዲን መምህር ሞገስ አሰፋ በበኩላቸው ቴክኖሎጂው ድርቅ እና የአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም፣ የመስኖ ውሃ ቴክኖሎጂ ለማዘመን እና ለማስፋፋት እንዲሁም የተሻሻለ ዝርያ ለማባዛት እና ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል።
በተያያዘ ዜና፤ ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የከብቶች እና በጎች ማድለብ ስራ አጠናክሮ እየሰራ ይገኛል።
*****//*****
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ሚያዝያ 04/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*****//*****