የዩኒቨርሲቲው የ2017 ዓ.ም ቁልፍ የአፈፃፀም አመላካቾች (KPI) ዕቅድ አፈፃፀም ለመገምገም የትምህርት ሚኒስቴር የሱፐርቪዥን ቡድን ዛሬ እሮብ ሚያዝያ 15/ 2017 ዓ/ም ወደ ራያ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ምልከታው ቁልፍ የአፈፃፀም ተግባራቱ ለመገምገም እና ለቀጣይ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ያለመ ነው።
ለ3ቀናት የሚቆየው ምልከታው የ2017 ዓ.ም የቁልፍ አፈፃፀም አመላካቾች ዕቅድ፣ አፈፃፀም ሪፖርት እና ሌሎች አስፈላጊ ሠነዶች በአካል ምልከታ የሚገመገሙ ሲሆን በዛሬው እለት የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ራያ ዩኒቨርሲቲ የሰራቸው ስራዎች አጭር ስእላዊ ማብራሪያ ለእንግዶቹ እና ለዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት አቅርበዋል።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ አባላት በቆይታቸው ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፣ ከየትምህርት ክፍሉ ከተወጣጡ መምህራን፣ ከአሰተዳደር ሰራተኞችና ከተማሪዎች ጋር ውይይቶችን እና በዩኒቨርሲቲው በመንቀሳቀስ የአካል ምልከታ ምልከታ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።









***************//***************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ሚያዝያ 15/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
***************//***************