በራያ ዩኒቨርሲቲ ብቃት እና ሰው ሃብት አሥተዳደር ሥራ አሥፈጻሚ ጽ/ቤት አዘጋጅነት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አዋጅ ቁጥር 1152/2011 እና አዲሱን የፌደራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 ለኮሌጅ ዲኖች፣ ዳይሬክተሮች፣ አስተባባሪዎች እና የትምህርት ክፍል ሀላፊዎች ግንቦት 08/ 2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ሰኔት መሰብሰቢያ አዳራሽ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
የዩኒቨርሲቲው ብቃትና ሰው ሃብት አሥተዳደር ሥራ አሥፈጻሚ አቶ ካሕሳይ ፍቃዱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አዋጅ ቁጥር 1152/2011 ፣ የከፍተኛ ትምህርት ምልመላ፣ ቅጥር እና ልማት መመሪያ ሕዳር 01/ 2011 እንዲሁም አዲሱን የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 መሰረት በማድረግ የሰራተኞች የደረጃ ዕድገት እና ዝውውር መመሪዎች ዝርዝር ገለጻ አድርገዋል።
በዩኒቨርሲቲው የሰው ሃብት አሥተዳደር በድን መሪ አቶ ብርሃኑ ግርማይ በበኩላቸው አዲሱን የፌደራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 መሰረት አድርገው የሥራ ሰዓትና ፍቃድ፣ የመንግሥት ሰራተኞች የግል መረጃ አያያዥ እና አደረጃጀት እና የመንግሥት ሠራተኞች ሥራ ውል ማቋረጥ እና ማራዘም የሚሉ አጀንዳዎች ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ከዲኖቹ፣ ዳይሬክተሮች እና ትምህርት ክፍል ሀላፊዎች ጋር በተደረገ ውይይት የተለያዩ ሀሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎች ተነስተው በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል።








***************//********************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ግንቦት 09/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት
********************//*************************