የአንደኛ አመት ተማሪዎች የመጀመርያ ቀን የመጀመርያ ትምህርታቸውን (Day one, Class one) ዛሬ ጀምረዋል።

የአቅም ማሻሽያ (Remedial) ትምህርታቸው በዩኒቨርሲቲያችን ተከታትለው ማለፍያ ነጥብ ያመጡ እና በ2018 የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር በራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ አድስ ገቢ ተማሪዎች የመጀመር ቀን የመጀመርያ ትምህርታቸው (Day One Class One) በተያዘለት የግዜ ሰሌዳ መሰረት ዛሬ ጥቅምት 17 ቀን፣ 2018 ዓ/ም ጀምረዋል።
የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ፤ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት ተወካይ መሓመድ አወል ዮሱፍ (ዶ/ር)፤ የምርምር፣ ማሕበረሰብ ጉድኝንት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተጠባባቂ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር መሓሪ ሃይለ (ዶ/ር)፤ የአካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተር መምህር ተስፋይ ሃረገወይን፤ እንዲሁም የትምህርት ጥራት መከታተያ ዳይሬክተር ብርሃነ ፀጋይ (ረ/ፕሮፌሰር) በአካል ተገኝተው መርሐ-ግብሩ ያስጀመሩ ሲሆን በትምህርት ገበታቸው ለተገኙ ሁሉም ተማሪዎችና በመማር ማስተማር ስራቸው ለነበሩ መምህራን የሰመረ የትምህርት ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸው ገልፀውላቸዋል።
የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ የመጀመርያ ቀን መጀመርያ ትምህርት (Day One, Class One) መርሐ-ግብሩን መጀመር አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት የመጀመርያ ቀን የመጀመርያ ትምህርት (Day One, Class One) አንዱ የራያ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ስራ ባህል ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው ተማሪዎቹ ከመጀመርያዋ የትምህርት ቀን ጀምሮው ምንም ግዜ ሳያባክኑ የመጡበትን የትምህርት አላማ ከግብ ለማድረስ ትምህርታቸው ጠንክረው ሊከታተሉ እንደሚገባ አሳስበዋል። አክለውም የመጀመርያ ቀን የመጀመርያ ትምህርት የሚለውን የመማር ማስተማር ስርዓት ትግበራ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ መምህራን እና ተማሪዎች፣ እንዲሁም ደግሞ ሌሎች ባለድርሻ አካላት የስራ ቅንጅት ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል።
በመጨረሻም ዩኒቨርሲቲያቸን ለተማሪዎቻችን መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛል።
================================
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
ራያ ዩኒቨርሲቲ
‎የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
‎**********
‎ የዩኒቨርሲቲያችን መረጃዎች ለማግኘት እነዚህን አማራጮች መጠቀም ይችላሉ:-
‎P.O. Box: 92, Maichew