የትምህርት ሚኒስቴር የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት በዩኒቨርሲቲው ሁለተኛ ቀን ቆይታቸው የ2017 ዓ.ም ቁልፍ የአፈፃፀም አመላካቾች ዕቅድ ትግበራ ለመገምገም፣ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ ከዩኒቨርሲቲው ከሁሉም የትምህርት ክፍሎች የተውጣጡ መምህራን እና ተማሪዎች፣ በተለያየ ደረጃ ከሚገኙ የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር በተያዘላቸው መርሃግብር መሰረት ውይይት አድርገዋል።
በተደረጉ ሶስት የተናጠል ውይይቶች የዩኒቨርሲቲው የ2017 ዓ.ም ቁልፍ የአፈፃፀም አመላካቾች ዕቅድ ትግበራ መሰረት በማድረግ የአስተዳደር እና ልማት፣ መማር ማስተማር ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስር እና ማህበረሰብ የአገልግሎት ዘርፍ የታዩ ጥንካሬዎችንና ክፍተቶችን እንዲሁም ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ተደርገው የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች ለመሰብሰብ ተችሏል።
በመርሃ ግብሩ መሰረት የልኡክ ቡድን አባላቱ ዛሬ ዓርብ ሚያዝያ 17/2017 ዓ.ም ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ጋር ውይይት ውይይት ከተደረጉ በኃላ የስራ ክፍሎችን የ2017 ዓ.ም የቁልፍ አፈፃፀም አመላካቾች ዕቅድ፣ አፈፃፀም ሪፖርት እና ሌሎች አስፈላጊ ሠነዶች ተንቀሳቅሰው የሚመለከቱ ይሆናል።

















***************//***************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ሚያዝያ 17/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
***************//***************