‎የዩኒቨርሲቲው በዞኑ የሚገኙ የስራ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት የፈጠራ ስራ ውድድር ሊያካሂድ መሆኑን ተገለጸ

‎የራያ ዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት የፈጠራ እና ብዜት ማእከል በደቡባዊ ትግራይ ዞን የፈጠራ ስራ ውድድር መርሀ ግብር አዘጋጅቶ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች ተወዳዳሪዎችን እየመዘገበ ይገኛል፡፡
‎የ2017 ዓ.ም የፈጠራ ስራ ውድድሩ በዩኒቨርሲቲው ስራ ፈጣሪ ተማሪዎች፣ ተመራማሪዎች እና ሰራተኞች እንዲሁም በዞኑ የሚሰሩ አዲስ ሀሳቦች፣ ተፅእኖ ፈጣሪ እና ችግር ፈቺ ፈጠራዎችን እውቅና ለመስጠት እና ለማስተዋወቅ የተነደፈ ሰፊ ውድድር ነው።
‎የውድድሩ ዓላማ የፈጠራ ባህልን በማሳደግ እና ታዳጊ ፈጣሪዎችን በመደገፍ የሚያጋጥሙ ችግሮችን የመፍታት አቅም ያላቸውን የላቀ ሀሳቦችን በመተግበር ለማህበረሰብና ሀገራዊ እድገት አስተዋፅዖ ለማበርከት ያለመ ነው።

Watch the video at the link below for more information. 

https://web.facebook.com/RayaUniversityOfficial/videos/1728473114408389

‎*****‎*****‎*****//*****‎*****‎*****‎*****
‎ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ግንቦት 12/ 2017 ዓ.ም
‎ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
‎የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት
‎*****‎*****‎*****‎*****//*****‎*****‎*****‎*****