የራያ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል አባላት የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም አመላካቾች (KPI) መሰረት በማድረግ በዝርዝር የቀረበውን የ2017 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ ዕቅድ ሀምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ገምግመዋል።
የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ የዩኒቨርሲቲው ዕቅድና ሪፖርት መሰረት በማድረግ በሰጡት ማብራሪያ የቁልፍ ተግባራት የአፈጻጸም አመላካቾች (KPI) መሰረት በማድረግ ስራዎቻችን እየሰራን መጥተናል በማለት በቀጣይም የዩኒቨርሲቲውን ከፍታ ለማስቀጠል ስራዎቻችን በብቃት በመስራት ጥንካሬዎቻችን አስቀጥለን ለሚያጋጥሙን ችግሮች ደግሞ ሁነኛ መፍትሄ በማስቀመጥ ዕቅዳችን ማሳካት ይጠበቅብናል ብለዋል።
ፕሮፌሰር ታደሰ አክለውም በዩኒቨርሲቲያችን በ2018 ዓ.ም አንድ ተጨማሪ የመምህራን መኖሪያ ህንፃ ለመገንባት፣ የባህል ማእከል ለማጠናከር፣ የላሞች፣ የዶሮ እና የንብ እርባታ ፕሮጀክቶች፣ የፍሳሽ ቆሻሻ ማከሚያ ስራዎች ለመስራት፣ የICT መሰረተ ልማት ዝርጋታ ለማስፋፋት እና የግቢ ውበት ስራዎች ለማጠናከር በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
ዶ/ር ነጋ ዓፈራ፤ በ2017 ዓ.ም የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም (KPI) መሰረት በማድረግ በመማር ማስተማር፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስር እና ማኅበረሰብ ጉድኝት ዘርፍ የተከናወኑ ቁልፍ እና ዓበይት ተግባራት፣ የነበሩ ጠንካራ ፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ለካውንስል አባላቱ ዝርዝር ገለጻ አድርገዋል።
የራያ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ክብሮም ካሕሱ በበኩላቸው የሰው ሀብት እና አስተዳደር ልማት ለማጠናከር፣ የዩኒቨርሲቲው መልካም ገጽታ ግንባታ ለማሳደግ፣ የህግ አገልግሎት ተደራሽነት ለማስፋፋት፣ የተማሪዎች አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ለማሻሻል፣ የግዥ ፍላጎትን በግዥ ዕቅድ መሰረት ለማሟላት፣ የጠቅላላ አገልግሎት ስርዓት ለማጠናከር፣ ፅዱ እና አረንጓዴ ግቢ ለመፍጠር፣ ተሽከርካሪ ጋራዥ ስምሪት ትራንስፖርት እና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ፣ ደኅንነቱ እና ጸጥታው የተጠበቀ ተቋም ለመፍጠር፣ ውጤታማ የንብረት አስተዳደር ስርዓት ለመዘርጋት እና ለማጠናከር፣ ገቢ የማመንጨት ዓቅምን ለማሳደግ፣ ውጤታማ እና ወጭ ቆጣቢ የሀብት አጠቃቀም ስርዓት ለመዘርጋት፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ለማስፋፋት፣ የውስጥ ኦዲት ስርዓት ለማጠናከር እና የዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን ተፈፃሚነት ለማሻሻል የተሰሩ ቁልፍ እና ዓበይት ተግባራት፣ የነበሩ ጥንካሬዎች፣ ተግዳሮቶች እና መፍትሔዎቻቸው እንዲሁም ለቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በዝርዝር አቅርበዋል።
የራያ ዩኒቨርሲቲ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ መ/ር ጋሻው ተፈሪ፤ የቁልፍ ተግባራት አፈጻጸም አመላካቾች (KPI) መሰረት በማድረግ የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ ዕቅድ በአራቱን ዕይታዎች ማለትም በመማርና ዕድገት፣ ፋይናንስ፣ የውስጥ አሰራር እና ደምበኞች ትኩረት አድርገው ቁልፍ እና ዓበይት ተግባራት፣ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶች እና መፍትሔዎች እንዲሁም ለቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በትንታኔ አቅርበዋል።
በተካሄደ ውይይት የካውንስል አባላቱ የተለያዩ ገንቢ አስተያየቶች እና ጥያቄች ያቀረቡ ሲሆን እንደ ዩኒቨርሲቲ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ሁሉም ማኅበረሰብ በየዘርፉ ተቀናጅቶ ውጤታማ ስራዎች መስራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
በመጨረሻም ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ሁሉም የዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች የ2018 ዓ.ም ዕቅድን ለማሳካት ተረባርቦና ተቀናጅቶ ተቋሙን የሚመጥን ውጤታማ ስራዎችን መስራት ይጠበቅብናል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።









**********//
**********
