የፌደራል ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከግንቦት 11-12/ 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለሚያካሂደው የሥነ ምግባር አምባሳደርነት ጥያቄና መልስ ውድድር በዩኒቨርሲቲው መጋቢት 06/ 2017 ዓ.ም በተደረገ ምልመላ መሰረት ተማሪ ካሕሳይ ሃይማኖት፣ ሐጎስ ታደሰ፣ መብራህቶም ገ/ሂወት፣ አብርሃ ሞገስ እና በርሀ ኪሮስ ራያ ዩኒቨርሲቲን በመወከል አዲስ አበባ ተገኝተዋል፡፡
ኮሚሽኑ በያዘው መርሃ ግብር መሰረት ከ47 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ ምዕራፎች በውድድር የተመለመሉ 235 ዕጩ የሥነ ምግባር አምባሳደርነት ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉ ሲሆን ተወዳዳሪዎቹ የጀማሪ፣ የተባባሪ እንዲሁም የከፍተኛ ደረጃ የሥነ ምግባር አምባሳደርነት ደረጃ የሚያገኙ ይሆናል።
በተጨማሪም ተወዳዳሪዎቹ በሶስቱም ምዕራፎች ለሚሰጠውን የዕውቀት፣ የክህሎት፣ የአመለካከት እና የሥነ ምግባር አቅም ግንባታ በብቃት ለሚያጠናቅቁ እና በ2017 ዓ.ም ክረምት በቤተሰብ-ተኮር የሥነ ምግባር ልማት ዙሪያ የበጎ ፍቃድ ሥራ ለሚሳተፉ “የሥነ ምግባር አምባሳደርነት” ሰርቲፊኬት ይሰጣል።
የማጠቃለያ ዙር ውድድሩ ግንቦት 12/2017 ዓ.ም የመንግሥት ከፍተኛ ባለ ሥልጣናት እና የባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ እንደሚካሄድ ከኮሚሽኑ ይፋዊ የማህበራዊ ድረ-ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
መልካም ዕድል ለተማሪዎቻችን!!!
***************//********************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ግንቦት 11/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት
*************************//********************