ከሚያዝያ 25 – 26/ 2017 ዓ.ም በራያ፣ አክሱም እና ዓዲ ግራት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል በተካሄደ የሳይንስ ሼርድ (Science Shared) ተማሪዎች የጥያቄ እና መልስ እና የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድሮች ራያ ዩኒቨርሲቲ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል።
በ9ኛ ክፍል የሳይንስ ሼርድ (Science Shared) ተማሪዎች መካከል በተካሄደ የጥያቄ እና መልስ ውድድር የራያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች 1ኛ እና 2ኛ ደረጃን ይዘዋል።
በተመሳሳይ ዜና በሶስቱም ዩኒቨርሲቲዎች መካከል በተካሄደ የ11ኛ ክፍል የሳይንስ ሼርድ (Science Shared) ተማሪዎች የጥያቄ እና መልስ ውድድር 1ኛ ደረጃን በራያ ዩኒቨርሲቲ ተይዟል።
በሶስቱም ዩኒቨርሲቲዎች መካከል በተካሄደ የሳይንስ ሼርድ (Science Shared) ተማሪዎች የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር ራያ ዩኒቨርሲቲ 1ኛ ደረጃን በመያዝ በድምር ውጤት አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል።
በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!











*****//*****
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ሚያዝያ 26/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*****//*****