የራያ ዩኒቨርስቲ የግብርና ኮሌጅ መምህራን፣ ተማራማሪዎች እና ባለሙያዎች በአዝርእት ብዜት፣ የመኖና እና እንስሳት የማደለብ ስራዎች እንዲሁም የንብ እርባታ ላይ እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ተገኝተው ሙያዊ ገለፃና ማብራርያ የሰጡ ሲሆኑ ጎብኝዎቹ አርሶ አድሮችና የዞኑ የግብርናና ገጠር ልማት ባለሙያዎችም በመስክ ጉብኝቱ በጣም እንደተደሰቱ ገልፀዋል።
በመርኃግብሩ ማገባዳጃ የአደራሽ ላይ ውይይት እና የምክክር መድረክ የነበረ ሲሆን ጎብኙዎች የነበሩዋቸው ኃሳብ አስተያየቶች አቅርበው በዩኒቨርስቲያችን ፕሬዚደንት ፕሮፌስር ታደሰ ደጀነ፣ የትግራይ ግብርና ቢሮኃላፊው እያሱ አብርሃ (ዶ/ር) እንዲሁም በዩኒቨርሲቲያችን የምርምር፣ ማሕበረሰብ አገልግሎትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተ/ምክትል ፕሬዚደንት መሓሪ ሃይለ (ዶ/ር) ማብራርያ ተሰጥታቸዋል።
======================================
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
ራያ ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
**********
የዩኒቨርሲቲያችን መረጃዎች ለማግኘት እነዚህን አማራጮች መጠቀም ይችላሉ:-
YouTube: https://www.youtube.com/@RAYAUNIVERSITY
Twitter: https://x.com/RayaUn2008
Website: https://www.rayu.edu.et/
P.O. Box: 92, Maichew

Users Last 7 days : 491
Users Last 30 days : 1783
Total Users : 24582