በራያ ዩኒቨርስቲ የግቢ ውስጥ ለውስጥ መስመር የWiFi ኔትዎርክ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ሲሰሩ የቆዩ የICT-መሰረተ ልማት ዝርጋታ እና ማስፋፍያ ስራዎች ተጠናቅቀው ትላንት ታህሳስ 03፣ 2018 ዓ/ም ተመርቀዋል።
የዩኒቨርሲቲያችን የአካደሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት ነጋ ዓፈራ (ዶ/ር) በምረቃ ስነ ስርዓቱ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን የኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽነት የዚህ ዘመን አንዱ መሰረታዊ ፍላጎት መሆኑን አውስተው ዩኒቨርሲቲው ለICT-የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ልዩ ትኩረት ስጠቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀው በስነ-ስርዓቱ በይፋ ለአገልግሎት ክፍት የተደረው ፕሮጀክትም የዚህ የትኩረት አቅጣጫ አንድ አካል መሆኑን አስረድተዋል። ዶ/ር ነጋ አክለውም ያልተጠናቀቁ የICT መሰረተ- ልማት ስራዎች በተቻለ ፍጥነትና ጥራት ለማጠናቀቅ የዩኒቨርሲቲው ማናጅመንት ቁርጠኛ መሆኑን አስረድተዋል።
የራያ ዩኒቨርሲቲ የICT ስራ-አስፈፃሚ መምህር ቢንያም ወ/ገብርኤል በበኩላቸው ለምረቃ የበቃው የWiFi ኢንተርኔት ዝርጋታ ፕሮጀክት እንዲሰራ አስተዋፅኦ ላደረጉ ድርጅቶች፤ የትምህርት ሚኒስቴር፣ የቴክኖሎጂ እና ኢንቬሽን ሚኒስቴር እንዲሁም ደግሞ የገንዘብ ድጋፍ ላደረገ የዓለም ባንክን አመስግነው የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ በሰፊ የሚንቀሳቀስባቸውና የሚሰበሰብባቸው ሁሉም የጊቢው ቦታዎች የነፃ WiFi-ኢንተርኔት እንደተገጠመባቸው ገልፀዋል። በተጨማሪም በተቀሩ የዩኒቨርስቲው የአገልግሎት ማእከላት እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የሚንቀሳቀስባቸው ቦታዎች ላይ ተጨማሪ የዝርጋታ ስራዎች በቀጣይ እንደሚሰሩ አስረድተዋል።
በራያ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ICT መሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራዎች ስያከናውን የቆየው የቴክኖሎጅ ድርጅት ተወካይ እና የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕሮጀክት አስተባባራ አቶ ሱራፊኤል ይበቃል በበኩላቸው በድርጅታቸው በኩል ለተሰራው ስራ ምስጋና ይሆን ዘንድ የምረቃ-ስነ ስርዓት መዘጋጀቱን በጣም እንዳስደሰታቸው ገልፀው ድርጅታቸው Cubeapux technology ለዩንቨርሲቲው ራዕይ እና ፍላጎት በሚመጥን መልኩ በፕሮጀክቱ ከተያዘው ዕቅድ በላይ እና ተጨማሪ የICT መሰረተ ልማት ዝርጋታ ቁሳቁሶ በማቅረብ አስተማማኝ የኢንተርኔት አገልግሎት ለዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ እንዲዳረስ ማድረጉን ገልፀዋል።
በመጨረሻም በICT መሰረተ-ልማት ዝርጋታ ትልቅ አስተዋፅኦ ላደረጉ የመንግስት መስርያ ቤቶች እና የራያ ዩኒቨርሲቲ የICT ስራ-አስፈፃሚ አባላት የምስጋና ምስክር ወረቀት፤ እንዲሁም ደግሞ ለCubeapux technology ባለሙያዎች ሙሉ የራያ ባህላዊ ልብስ እንደስጦታ በማበርከት መድረኩ ተጠናቅቀዋል።
==================================
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
ራያ ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
*****************************
የዩኒቨርሲቲያችን መረጃዎች ለማግኘት እነዚህን አማራጮች መጠቀም ይችላሉ:-
YouTube: https://www.youtube.com/@RAYAUNIVERSITY
Twitter: https://x.com/RayaUn2008
Website: https://www.rayu.edu.et/
P.O. Box: 92, Maichew

Users Last 7 days : 738
Users Last 30 days : 2472
Total Users : 26738