በራያ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ዛሬ ሀምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐግብር ተካሄዷል::
የራያ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ በየዓመቱ የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ምክንያት በማድረግ የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ታደሰ ደጀኔ (ፕሮፈሰር)፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ነጋ ዓፈራ፣ የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ክብሮም ካሕሱን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በዘንድሮውን የችግኝ ተከላ መርሐግብሩ ተሳትፈዋል።
በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለሚከሰቱ የተለያዩ የተፈጥሮ አደጋዎች በዘላቂነት ለመከላከል ውጤታማ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ የገለጹት የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ዩኒቨርሲቲያንም ይህን ለመተግበር የራሱን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል::





















*****//*****
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ሀምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
*****//*****