በሰላም እና በስኬት ተጠናቀቀ

‎ከሰኔ 23 እስከ ሀምሌ 08/ 2017ዓ.ም በራያ ዩኒቨርሲቲ በወረቀት እና በበይነመረብ (Online) የተሰጠ ሀገር አቀፍ የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በሰላም እና በስኬት ተጠናቀቀ።
‎በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ በወረቀት የተሰጠ የ12ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 – 25/ 2017 ዓ.ም ሲሆን፤ በበይነ መረብ (Online) ደግሞ ከሰኔ 26 – 30/ 2017 ዓ.ም ተሰጥቷል።
‎የ12ኛ ክፍል የማኅበራዊ ሳይንስ ፈተና ተፈታኞች በበኩላቸው ከሀምሌ 01 – 03/ 2017 ዓ.ም በወረቀት፤ ከሀምሌ 04 – 08/ 2017 ዓ.ም በበይነ መረብ ፈተናቸውን ወስደዋል።
‎ፈተናውን በተሳካ መንገድ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱት አካላት ዩኒቨርሲቲው የላቀ ምስጋናውን ለማቅረብ ይወዳል።
‎ተፈታኝ ተማሪዎችም ፈተናው ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ላሳዩት የላቀ ስነ- ምግባር እያመሰገነ መልካም ዕድል እንዲገጥማቸው ዩኒቨርሲቲያችን ምኞቱን ይገልጻል፡፡
‎*****//*****
‎ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ሀምሌ 08 ቀን 2017 ዓ.ም
‎ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
‎የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
‎*****//*****