ህዳር 27፣ 2018 ዓ/ም (ራያ ዩኒቨርሲቲ)
በራያ ዩኒቨርሲቲ የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል በማስመልከት የውይይት እና የቃል-ኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት ማስጀመርያ መድረክ ተካሄደ። በመድረኩ የራያ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አመራር አባሉ ሓለፎም ገዛኢ (ዶ/ር)፣ የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ፣ ጊዜያዊ የማይጨው ከተማ ከንቲባ መምህር ጌታቸው፣ የሀይማኖት ተወካዮችና የሀገር ሽማግሌዎች ጨምሮ በርካታ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና ማኅበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።
የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት ጠንካራ መልዕክት፣ “ብዙ ባህሎች፣ ቋንቋዎችና አስተሳሰቦች ባሉበት ሀገር ውስጥ ሆነን ልዩነቶችን ተቀብለን አንድ የሚያደርገንን ፍቅር ከመመሥረት ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም” ብለዋል። ፕሮፌሰር አክለውም ዩኒቨርሲቲዎች መልክ የሚኖራቸው ተማሪዎች አስተምረው ስለ የምያስመርቁ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ብሔረ ብሄረሰቦች፣ ሕዝቦች፣ አስተሳሰቦች እና ሙያዊ አደረጃጀቶች አሰባስቦው የሚይዙ ተቋማት ሲሆኑም ጭምር ነው በማለት የብዝኃነትን ፋይዳ በአጽንኦት ተናግረዋል።
የራያ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አመራር አባሉ ሓለፎም ገዛኢ (ዶ/ር) በበኩላቸው በዩኒቨርሲቲው ተገኝተው የቃል-ኪዳን ቤተሰብነትን መጋራት በመቻላቸው የተሰማቸው ደስተ ገልፀው፤ ዩኒቨርሲቲ ብዙሃን የሚገለገሉበት የመንግስት ተቋም እንደመሆኑ መጠን ሁኔታዎች ባልተመቻቹበት በአስቸጋሪው ወቅትም ቢሆን የብሄር ብሄረሰቦች ብዓል መከበር እንዳለበት አስረድተዋል።
የራያ ዩኒቨርሲቲ የአከዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት ነጋ ዓፈራ (ዶ/ር) የብሄርና ብሄረሰቦች ብዓል ምንነት እና የብዓሉን አከባበር ለአገራዊ ኢኮኖሚ የሚኖሮው ፋይዳ በተመለከተ፤ እንዲሁም በራያ ዩኒቨርሲቲ የራያ ባህል ምርምር ማእከል ዳይሬክተር የሆኑት ገሰሰ ንጉስ (ዶ/ር) ደግሞ “የቃል-ኪዳን ቤተሰብ” የፕሮጀክት ማስጀመርያ እና የባለ-ድርሻ አካላት ዝርዝር ሚና የሚዳስስ፤ የመወያያ ፅሑፎች አቅርበዋል።
የቃል-ኪዳን ቤተሰብ ፕሮጀክት በዋናነት የሚያተኩረው፥ ቤተሰቦቻቸውን ትተው ወደ ዩኒቨርሲቲ ለሚመጡ ተማሪዎች፣ ዩኒቨርሲቲው በሚገኝበት አካባቢ ያለው ማኅበረሰብ እንደ አባትና እናት ሆኖ የወላጅነት ፍቅር እንዲሰጣቸውና የማኅበረሰቡ አባል ሆነው ተመርቀው እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑ ተገልጿል። ይህ ፕሮጀክት ተማሪዎች የሚገጥማቸው ትምህርታዊ ውጥረት የሚያቃል ማኅበራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ያግዛል ተብሎ ይታመናል።
በመጨረሻም የመድረኩ ተሳታፊዎች በቀረቡ የመወያያ ፅሑፎች እና አጠቃላይ የብዓሉ መንፈስ በተመለከቱ ገንቢ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች የሰጡ ሲሆን በጊዝያዊው የማይጨው ከንቲባ መምህር ጌታቸው፣ የራያ ዩኒቨርስቲ ቦርድ አመራር ሓለፎም ገዛኢ እና በፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ በኩል ምላሽ እና ማብራርያ ተሰጥቶባቸው መድረኩ ተጠናቅቀዋል።
=======================================
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
*****//*****
የዩኒቨርሲቲያችን መረጃዎች ለማግኘት እነዚህን አማራጮች መጠቀም ይችላሉ:-
YouTube: https://www.youtube.com/@RAYAUNIVERSITY
Twitter: https://x.com/RayaUn2008
Website: https://www.rayu.edu.et/
P.O. Box: 92, Maichew

Users Last 7 days : 738
Users Last 30 days : 2472
Total Users : 26738