በራያ ዩኒቨርሲቲ ከሰኔ 02-10/ 2017 ዓ.ም የተሰጠው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) በስኬት ተጠናቀቀ

‎ከሰኔ 02/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በራያ ዩኒቨርሲቲ መሰጠት የጀመረው የከፍተኛ ትምህርት ቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ተማሪዎች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ሰኔ 10/ 2017 ዓ.ም በሰላም እና በስኬት መጠናቀቁን ተገለጸ።
‎የራያ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ዳይሬክተር መምህር ብርሃነ ፀጋይ (ረዳት ፕሮፌሰር) የመውጫ ፈተናው በስኬት መጠናቀቁን አስመልክተው ባስተላለፉት መልእክት፤ ፈተናው በሰላም እና በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱት የትምህርት ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት አባላት፣ የዩኒቨርሲቲው የፈተና ግብረሃይል፣ ለፈታኝ መምህራን፣ ለአይ ሲ ቲ ባለሙያዎች፣ ለግቢ ሰላምና ደህንነት ሰራተኞች፣ በጥሩ ዲሲፕሊን ፈተናውን ላጠናቀቁ ተፈታኝ ተማሪዎች፣ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
‎ዩኒቨርሲቲው ለፈተናው ሂደት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ እና ግብአት በማሟላት እንዲሁም ስለ ፈተና ሂደት ሕግ እና ደምብ አጠቃላይ ገለጻ (Orientation) በማድረግ ፈተናው ሰለማዊ በሆነ መንገድ እንዲሰጥ አስችሏል ያሉት የፈተናዎች ማእከል አስተባባሪ መምህር ተስፋይ ሀረገወይን፤ የመውጫ ፈተናው በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱት አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
‎ዩኒቨርሲቲው ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ምኞቱን ይገልጻል!
‎*****‎*****‎*****//‎*****‎*****‎**********
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም
‎ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
‎የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
‎*****‎*****‎*****//‎*****‎*****‎**********