ጥቅምት 24፣ 2018 ዓ/ም (ራያ ዩኒቨርሲቲ)
በራያ ዩኒቨርሲቲ የተቋማዊ ለውጥ ሥራ አስፈፃሚ አዘጋጅነት ለሁለት ተከታታይ ቀናት (ከጥቅምት 22 – 23፣ 2018 ዓ/ም) ከትምህርት ሚኒስቴር በመጡ አሰልጣኞች ለዩኒቨርስቲው መካከለኛ አመራሮች በመኾኒ ከተማ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ። የዩኒቨርሲቲያችን የአካደሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት ነጋ ዓፈራ (ዶ/ር) በስልጠናው ቦታ ተገኝተው ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር ከትምህርት ሚኒስቴር ለመጡ አሰልጣኞች አመስግነው ስልጠናው ራያ ዩኒቨርሲቲ እያከናወናቸው ላሉ የሪፎርም ስራዎች ትልቅ አስተዋፅኦ ያለው በመሆኑ ሁሉም ሰልጣኞች በትኩረት እንዲከታተሉት አፅንኦት ስጠተዋል።
ይህ ስልጠና በትምህርት ሚኒስቴር የተቋማዊ ለውጥ ስራ አሰፈፃሚ አቶ ከበደ ግዛው እና የስልጠና ባለ ሙያ የሆኑት አቶ ዘገየ የተሰጠ ሲሆን አራት አበይት አርእስቶችን ያካተተ ነበር። በተቋማዊ ለውጥ ዙርያ የሚያተኩረው ይህ ስልጠና፤ የከፍተኛ ትምህርት የለውጥ ስራዎች፤ የሰራተኛች ብቃትና ምዘና፤ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርአት፤ እንዲሁም የስራ አመራር ስነ-ምግባር በሚሉ አራት አርእስቶች ሲፊ ገለፃና ውይይት ተደርጓል።
በስልጠናው የመዝግያ ንግግር ያሰሙት በራያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር፣ ማሕበረሰብ ጉድኝንትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ተ/ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር መሓር ሃይለ (ዶ/ር) በበኩላቸው ስልጠናው በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እየተሰሩ ያሉ የሪፎርም ስራዎችና ለወደፊት በመንግስት በኩል የተቀመጡ አቅጣጫዎች ምን እንደሚመስል የሚያሳይና ከራያ ዩኒቨርስቲ አንፃር ሲታይም ምን እና ምን የሪፎርም ስራዎች እንደሚጥበቁብን የሚጠቁም ስልጠና እንደነበረ ገልፀው ስልጠናውን ለሰጡ አሰልጣኞችም አምስግነዋል።
በስተመጨረሻም የአካደሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንቱ ነጋ ዓፈራ (ዶ/ር) የዩኒቨርስቲያችንን ፕሬዚደንት በመወከል ለአሰልጣኞች የራያ ባህላዊ ልብስ በስጦታ መልክ የሰጡ ሲሆን አሰልጣኞቹ በቀጣይ ራያ ዩኒቨርሲቲን እንዲደግፉና ያላቸውን ግንኙነት እንዲያጠነክሩ ዘንድ አደራ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቅቀዋል።
================================
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
ራያ ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
**********
የዩኒቨርሲቲያችን መረጃዎች ለማግኘት እነዚህን አማራጮች መጠቀም ይችላሉ:-
YouTube: https://www.youtube.com/@RAYAUNIVERSITY
Twitter: https://x.com/RayaUn2008
Website: https://www.rayu.edu.et/
P.O. Box: 92, Maichew

Users Last 7 days : 493
Users Last 30 days : 1785
Total Users : 24584