(ራያ ዩኒቨርሲቲ፤ ሕዳር 15 ቀን 2018 ዓ/ም)
ራያ ዩኒቨርሲቲ የግብርናውን ዘርፍ ለማስፋፋት እና ለማዘመን አልሞ የተለያዩ የምርምር፣ የማኅበረሰብ ጉድኝት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በ18 ሄክታር የምርምር ማሳ ላይ ያፈራውን “ቦሩ” የተሰኘ የስንዴ ምርጥ ዘርም አባዝቶ ለአርሶአደሮች እና ተጠቃሚዎች ተደራሽ ለማድረግ በተቀናጀ መልኩ እየሰራ ይገኛል።
የዩኒቨርሲቲያችን የአስተዳደርና ልማት ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት ክብሮም ካሕሱ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ከዚህ የምርጥ ዘር ብዜት ስራ ጎን ለጎን ለማረሻ፣ መዝሪያ፣ ማጨጃ እና ለመውቅያ የሚያገለግሉ አዳዲስ ማሽኖች በማስገባት የግብርና ዘርፉ በማዘመን፣ ምርታማነት በማሳደግ፣ እንዲሁም የግብርና ቴክኖሎጂዎች እንዲስፋፉና የአከባቢው አርሶ-አደሮች እንዲላመዱዋቸው በማድረግ በኩል ውጤታማ ስራ እየሰራ እንደሚገኝና አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት አፅንኦት ሰጠውበታል።
የራያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር፣ ማኅበረሰብ ጉድኝት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር መሓሪ ሃይለ (ዶ/ር) በተመሳሳይ በሰጡት ኃሳብ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት የሚያሳድጉ ጥራት ያላቸው፣ ጊዜ የሚቆጥቡ፤ የስራ ማስኬጃ ወጪቺዎችና የሰው ሃይል ብክነት የሚቀንሱ የቅድመ እና ድህረ-ምርት ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለማኅበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ፤ እንዲሁም የማኅበረሰቡ ለውጥ ለማረጋገጥ ከተለያዩ የምርምር ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
የራያ ዩኒቨርሲቲ የግብርና እና ተፈጥሮ ሃብት ኮሌጅ ዲን የሆኑት መምህር ሞገስ አሰፋ በበኩላቸው ራያ ዩኒቨርሲቲ ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በእንስሳት እርባታ፤ የአዝርእት እና አትክልትና ፍራፍሬ ምርጥ ዘር ብዜት፣ የእንስሳት መኖ አቅርቦት፣ እንዲሁም የአፈርን ለምነት ለማስጠበቅ የሚያግዙ ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለማኅበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል በማለት ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።
በግብርና ስራ ሂደቱ እየተሳተፉ ያገኘናቸው አርሶ አደሮች በበኩላቸው ራያ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ምርት እና ምርታማነት ለማሳደግ የተለያዩ ውጤታማ ስራዎች እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው አርሶ አደሩን ተጠቃሚ የሚያደርጉ መሰል የግብርና እና የግብርና ቴክኖሎጂ ማስፋፍያ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ኃሳባቸው ሰጥተዋል። አርሶ አደሮቹ አክለውም የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ ከተለመደው አሰራር መውጣት፣ የምርት ስብጥሩን ማስፋትና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት መጠቀም እንደሚገባ መገንዘባቸውን አስረድተዋል።
**************************************
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
*****//*****
የዩኒቨርሲቲያችን መረጃዎች ለማግኘት እነዚህን አማራጮች መጠቀም ይችላሉ:-
YouTube: https://www.youtube.com/@RAYAUNIVERSITY
Twitter: https://x.com/RayaUn2008
Website: https://www.rayu.edu.et/
P.O. Box: 92, Maichew

Users Last 7 days : 738
Users Last 30 days : 2472
Total Users : 26738