ህዳር 26፤ 2018 ዓ/ም (ራያ ዩኒቨርሲቲ)
በ2018 የትምህርት ዘመን በራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የአቅም ማሻሽያ መርኃ-ግብር (Remedial Program) ተማሪዎች ከህዳር 22 ጀምረው ወደ ዩኒቨርሲቲው የገቡ ሲሆን፣ ቅበላው ህዳር 24፣ 2018 ዓ/ም በተዘጋጀው ደማቅ የእንኳን ደህና መጣቹ መድረክ ፍፃሜው አገኝተዋል።
የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ በመድረኩ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣቹ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ፕሮፌሰር በመልእክታቸው ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎቹ ተቀብሎ በሚገባ አስተምሮ ለውጤት በማብቃት በሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የሚደነቅ ብቃቱ ያሳየ ተቋም መሆኑን አወስተው በቀጣይም አድስ ገቢዎቹ ተማሪዎች በተሻለ ምቾታቸውን አስጠብቆና እውቀትን አስታጥቆ ህዝብና ሀገር የሚያገለግሉ ዜጎችን ለማፍራት ዝግጁ መሆኑን አብራርተዋል።
የዩኒቨርሲቲያችን የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚደንት ነጋ ዓፈራ በበኩላቸው በመድረኩ ተግኝተው ተማሪዎቹ ሙሉ ግዚያቸው ለመጡበት የትምህርት ዓላማ ብቻ እና ብቻ እንዲያውሉት የመከሩ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ እና ትውልድን ለማነፅ እያደረጋቸው ያሉ ዘርፈ-ብዙ ስራዎች እና ዝግጅቶች በተመለከተም ገለፃ አድርገዋል።
በመጨረሻም በተለያዩ የመድረክ ሙዚቃዎች እና ውዝዋዜዎች ደምቆ በዋለው በዚህ መድረክ ባለፈው የ2017 ትምህርት ዘመን ክፍተኛ ውጤት ያመጡ የሁሉም ኮሌጆች ነባር ተማሪዎች የእውቅና ሰርቲፊኬት እና የመበረታቻ ሽልማት በማበርከት ተጠናቅቀዋል።
=================================
ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
ራያ ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
**********
የዩኒቨርሲቲያችን መረጃዎች ለማግኘት እነዚህን አማራጮች መጠቀም ይችላሉ:-
YouTube: https://www.youtube.com/@RAYAUNIVERSITY
Twitter: https://x.com/RayaUn2008
Website: https://www.rayu.edu.et/
P.O. Box: 92, Maichew

Users Last 7 days : 738
Users Last 30 days : 2472
Total Users : 26738