ራያ ዩኒቨርሲቲ እና ፋና ወጣቶች የብድርና ቁጠባ ተቋም ለዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች የረዥም ግዜ የብድር አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የመግባብያ ሰነድ ተፈራረሙ!

ህዳር 28፣ 2018 ዓ/ም (ራያ ዩኒቨርሲቲ)
ራያ ዩኒቨርሲቲ የሰራተኞቹ ኑሮ ለማሻሻል የሚረዳ የቁጠባና የብድር አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችል የመግባብያ ሰነድ ከፋና ወጣቶች የብድርና ቁጠባ አክስዮን ማሕበር ጋር ዛሬ ህዳር 28፣ 2018 ዓ/ም ተፈራርመዋል። የራያ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አመራር አባል እና የፋና የብድርና ቁጠባ ተቋም ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ሓለፎም ገዛኢ (ዶ/ር) በፌርማ ስነ-ስርዓቱ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት ሁለቱም ተቋሞች በትብብር የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ኑሮ ለማሻሻል ለመስራት ቁርጠኛ መሆናን አንዳለባቸው መልእክታቸው አስተላልፈዋል ።
ራያ ዩኒቨርሲቲን ወክለው የስምምነት ሰነዱን የፈረሙት የራያ ዩኒቨርስቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት እና የዩኒቨርስቲው የፕሬዚደንት ተወካይ ነጋ ዓፈራ (ዶ/ር) በሰጡት ሃሳብ ዩኒቨርሲቲው በተለይም ከ2017 ዓ/ም ጀምሮ ምቹ የስራ ሁኔታ ለመፍጠርና የሰራተኞቹ ኑሮ ለማሻሻል በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው ከፋና የቁጠባ እና ብድር ተቋም ጋር የተደረገው ስምምነትም የዚህ ጥረት አንድ አካል መሆኑን አብራርተዋል። የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች በቁጠባ ተቋሙ ከመቆጠብና የተለየ የብድር አገልግሎት ከማግኘትም ባለፈ ራያ ዩኒቨርሲቲ እና ፋና ወጣቶች የቁጠባና ብድር ተቋምበ ትምህርት፣ በምርምር፣ በማሕበረሰብ አገልግሎቶችና በቴክኖሎጂ ሽግግር አብረው ለመስራት የሚያስችል ሰነድ መሆኑን የገለፁት ነጋ ዓፈራ (ዶ/ር ) ለስምምነቱ ተፈጻሚነትም ራያ ዩኒቨርሲቲ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል ።
ፋና ወጣቶች የቁጠባና ብድር ተቋም ውክለው ስምምነቱን የፈረሙት ደግሞ የተቋሙ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጎይቶኦም ተስፋይ አሰፋ ሲሆኑ ፋና ወጣቶች የቁጠባና ብድር አክስዮን ማህበር በስምምነት ሰነዱ የፈረማቸውን ዝርዝር ነጥቦች ለመፈፀም ቁርጠኛ መሆኑ አብራርተው፤ ሌሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞችም የራያ ዩኒቨርሲቲ ፈለግ ተከትለው የሰራተኞቻቸው የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል ከተቋማቸው አብረው እንዲሰሩና መሰል ስምምነቶች ከፋይናንስ ተቋሙ ጋር ሊዋዋሉ እንደሚገባ ገልፀዋል።
የፌርማ ስነ-ስርዓቱ የተካሄደው የራያ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች እና የፋና ወጣቶች የቁጠባና ብድር ተቋም የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው።
==================================
‎ዕውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
‎የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
‎*****//*****
‎የዩኒቨርሲቲያችን መረጃዎች ለማግኘት እነዚህን አማራጮች መጠቀም ይችላሉ:-
‎P.O. Box: 92, Maichew