የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ አመራሮች እና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች በዩኒቨርሲቲው እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ አገልግሎቶች የሚሰጡ ግንባታዎች እና የመሰረተ ልማት ስራዎች ጉብኝት አደረጉ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ አመራሮች እና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች በዩኒቨርሲቲው እየተሰሩ ያሉ
  • የተማሪዎች መማርያ፣
  • መኝታ እና ልብስ ማጠብያ ህንፃዎች (Laundry)፣
  • የመመረቅያ እና መመገብያ አዳራሽ፣
  • ዘመናዊ የበግ እና ከብት ማድለብያ እና እርባታ ቦታ (Shade)፣
  • የመንገድ ዝርጋታ፣
  • የግቢ ውበት እና ተፋሰስ ስራዎች
  • እንዲሁም የግብርና ምርምር ማእከላት ዛሬ መጋቢት 26/2016 ዓ/ም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
የጉብኝቱ ዋና ዓላማ በዩኒቨርሲቲው እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ አገልግሎቶች የሚሰጡ ግንባታዎች እና መሰረተ ልማት ስራዎች ለመከታተል እና አስፈላጊውን ድጋፍ በመስጠት በተያዘላቸው የግዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቁ ለማስቻል ነው፡፡
በጉብኝቱ ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ (የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት)፣ አቶ ሃፍቱ ኪሮስ (የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አባል)፣ ዶ/ር ክብሮም ካሕሱ (የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት)፣ ዶ/ር ነጋ ዓፈራ (የዩኒቨርሲቲው አካ/ ምር/ ቴክ/ሽግ/ማህ/አገ ምክ/ፕረዚደንት) እና የዩኒቨርሲቲው ፕሮጀክት ግንባታ ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡
*********************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
መጋቢት 26/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*********************************