የዓዲ ግራት ዩኒቨርሲቲ የሠራተኞች የሥራ ድልድል ኮሚቴ አባላት ከዩኒቨርሲቲው ልምድ ቀሥመዋል።

ራያ ዩኒቨርሲቲ የሠራተኞች ድልድል መመርያዎች መሠረት በማድረግ የድልድል እና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች አዋቅሮ በሠራተኞች ድልድል፣ የሠራተኞች ሥራ ልምድ፣ ትምህርት ዝግጅት እና ሥራ አፈፃፀም ምዘና አያያዝ ስርዓት እንዲሁም የሠራተኞች ቅሬታ ማስተናገጃ ሥርዓት በተመለከተ የዓዲ ግራት ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች የሥራ ድልድል ኮሚቴ አባላት ዛሬ ጥር 28/2016 ዓ/ም ልምድ ቀስመዋል።
የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ክብሮም ካሕሱ (ዶ/ር) ለእንግዶቹ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት አዲሱ የዩኒቨርሲቲያችን ሠራተኞች የሥራ ድልድል መዋቅር ሰኔ 11/2015 ዓ/ም በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ፀድቆ ከሠራተኞቻችን ጋር ከመስከረም 09/2016ዓ/ም ጀምረን የተለያዩ ውይይቶች በማካሄድ ክፍት የሥራ ማስታወቂያ አውጥተን ሠራተኞች በሚመለከተው የሥራ መደብ እንዲወዳደሩ እና ከሥራ ድልድሉ በኋላ ቅሬታ ያለባቸው ሰራተኞች በመመርያው መሰረት ቅሬታቸው እንዲስተናገድ አድርገን ወደ ሥራ ገብተናል ብለዋል።
የዓዲ ግራት ልኡካን ቡድን አባላት በበኩላቸው በተደረገላቸው መልካም አቀባበል አድንቀው የተደረገላቸው የሥራ ድልድል መመርያዎች ገለፃ ለቀጣይ ሥራቸው አጋዥ ነው ብለዋል።
የልኡካን ቡድኑ አባላት አክለው ይህ መልካም ልምድ ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች አርአያ ሊሆን ይገባል በማለት ሀሳባቸውን አጋርተዋል።
***********************
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
👇👇👇
Facebook: https://www.facebook.com/Raya University