የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የመሩት ልኡክ ቡድን አባላት በዩኒቨርሲቲው እየተገነቡ ያሉ የመሰረተ ልማት ስራዎች ጎበኙ፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ከፍተኛ አመራር ቡድን በራያ ዩኒቨርሲቲ እየተከናወኑ የሚገኙ የግንባታ ፕሮጀክት ላይ የመስክ ምልከታ ለማድረግ ማይጨው ከተማ ሲገባ በዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ የተመራ ቡድን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡በ2016 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው ከ900 ሚልየን ብር በላይ በጀት ተመድቦላቸው እየተገነቡ ያሉ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች ማለትም የተማሪዎች መማርያ፣ መኝታ እና የልብስ ማጠብያ ህንፃዎች፣
የውሃ፣ መብራት፣ መንገድ እና ፍሳሽ ማስወገጃ ስራዎች፣ የአጥር ግንባታ እንዲሁም የስብሰባ አዳራሽ እና የተማሪዎች መመገብያ ባንድ ላይ የያዘ ዘመናዊ አዳራሽ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለ ስልጣን ዋና ዳይሬክተር በተከበሩ ኢ/ር መስፍን ነገዎ የተመራ ልኡክ ቡድን አባላት ዛሬ ሰኔ 09/2016 ዓ/ም ጉብኝት አድርገዋል፡፡
የጉብኝቱ ዋና ዓላማ በዩኒቨርሲቲው እየተገነቡ ያሉ የመሰረተ ልማት ስራዎች በጋራ ለማየት እና እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች ላይ ውይይት በማድረግ የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው፡፡
በጉብኝቱ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን መስሪያ ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች፣ ኮንትራክተሮች እና የግንባታ ባለሙዎች ተሳትፈዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ለልኡካን ቡድኑ አባላት ዩኒቨርሲቲው እንዲገነባ የመሰረት ድንጋይ ከተቀመጠለት ከየካቲት 08/2008 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 2016 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው የተገነቡ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች አጭር ሪፖርት እና ገለፃ አቅርበዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ዩኒቨርሲቲውን ፅዱ፣ ውብ እና አረንጓዴ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ውጤታማ ስራዎችን ለማጠናከር የልኡክ ቡድኑ አባላት በዩኒቨርሲቲው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሂደዋል፡፡
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ እንደተናሩት በራያ ዩኒቨርሲቲ እየተገነቡ ያሉ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች ለሁሉም የመንግስት ተቋማት አርአያ የሚሆን እና ዩኒቨርሲቲው ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ትልቅ አስተዋፅኦ ስለሚኖራቸው ግንባታዎቹ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ የሁሉም ሰራተኛ ጥንካሬ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
*****************************
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*****************************
ለበለጠ መረጃ👇👇👇ይመልከቱ።