በራያ ዩኒቨርሲቲ ግሪን ሀውስ ለመገንባት የትግራይ ባዮ ቴክኖሎጂ ማዕከል የንድፈ ሀሳብ ገለፃ አድርጓል።

ራያ ዩኒቨርሲቲ እና የትግራይ ባዮ-ቴክኖሎጂ ማዕከል ጥቅምት 17/2016 ዓ/ም በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ግብርና ልማት፣ ኢንደስትሪ ተኮር የግብርና ሥራዎች፣ ግሪን ሃውስ ቴክኖሎጂ በሰው ሀብት ልማትና ዙርያ አብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን የጋራ መግባብያ ሰነድ (MoU) በተፈራረሙት መሰረት ዛሬ ጥር 28/2016 ዓ/ም በግብርና ምርምር እና ልማት ዘርፍ ያለውን ልምድ እና ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ በራያ ዩኒቨርሲቲ የግሪን ሀውስ ለመገንባት የሚያስችለውን ንድፈ ሀሳብ በማእከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃፍታይ ኣባዲ ለሚመለከታቸው አካላት ገለፃ አድርገዋል።
የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ነጋ ዓፈራ እንደገለፁት በዩኒቨርሲቲያችን የሚገነባውን የግሪን ሀውስ ፕሮጀክት የተለያዩ የምርምር ውጤቶች በማምጣትና የተፈጥሮ ሚዛን በመጠበቅ ለመማር ማስተማር ሂደት፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም ማህበረሰቡን ለመጥቀም ስለሚያግዝ በሚመለከተው አካል ፀድቆ ወደ ተግባር እንደሚገባ ተናግረዋል።
በንድፈ ሀሳብ ገለፃ ከተሳታፊዎች ለተነሱ የተለያዩ ሀሳቦች፣ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች በሚመለከታቸው አካላት ማብራርያ ተሰጥቷል።
***********************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ጥር 28/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
👇👇👇