በራያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ባለሙያዎች የበለፀጉ ሶስት መተግበሪያዎች በድምቀት ተመረቁ።

መንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን ዲጂታል በማድረግ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በራዩ መምህራን እና ባለሙያዎች የበለፀጉ የንብረት አስተዳደር መረጃ ስርዓት (Property Management Information System)፣ የራዩ ድህረ ገፅ (RU’s Website) እና የፈተና አስተዳደር ስርዓት ፖርታል (Exam Administration System Portal) የደቡባዊ ትግራይ ዋና አስተዳዳሪ እና የራዩ ሥራ አመራር ቦርድ አባል አቶ ሃፍቱ ኪሮስ፣ የራዩ ፕረዚደንት፣ ሁለቱም ምክትል ፕረዚደንቶች፣ የካውንስል አባላት እና ማህ/ብ በተገኙበት ሚያዝያ 04/2016 ዓ/ም በድምቀት ተመረቁ።
ፕ/ር ታደሰ ደጀኔ በመክፈቻ ንግግራቸው ራዩ በአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ግንባታ እና መሰረተ ልማት ዝርጋታ እየሰራቸው ያሉ ውጤታማ ስራዎች የሚታወቅ ሲሆን ራዩ ዲጂታላይዝ ለማድረግ በውስጥ ዓቅም የበለፀጉ ዘመናዊ መተግበሪያዎች ለምረቃ መብቃታቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
የበለፀገው የራዩ ንአመስ መተግበሪያ በአቶ ሃፍቱ ኪሮስ እና ፕ/ር ታደሰ ደጀኔ ስራውን በይፋ ያስጀመሩት ሲሆን ባለሙያው መ/ር ሙላታ ከበደ የአዲሱ መተግበሪያ ዲጂታል የንብረት አስተዳደር ስርዓት በመተግበር ብክነት ለመቀነስ ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ያለመ ነው ብለዋል። የበለፀገው መተግበሪያ ለሚመለከተቻው አካላት ታህሳስ 10/2016 ዓ/ም ገለፃ ተደርጎ መገምገሙን ይታወሳል።
የራዩ ድህረ ገፅ (RU’s Website) መተግበሪያ በአቶ ሃፍቱ ኪሮስ እና ፕ/ር ታደሰ ደጀኔ ስራውን በይፋ ያስጀመሩት ሲሆን ባለሙያው መ/ር ገብርየ እምባፍረሱ አጭር ገለፃ አድርገዋል። የበለፀገው መተግበሪያ ለሚመለከተቻው አካላት ህዳር 28/2016 ዓ/ም ገለፃ ተደርጎ መገምገሙን ይታወሳል።
የራዩ ፈአስፖ መተግበሪያ በዶ/ር ነጋ ዓፈራ እና በዶ/ር ክብሮም ካሕሱ ስራውን በይፋ ያስጀመሩት ሲሆን የዘርፉ ባለሙያ መ/ር የማነ ገ/ስላሴ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ጥራት ያለው እና ብክነት የሚቀንስ የፈተና ስርዓት እንዲኖረን ይረዳል ብለዋል። ከዚህ በፊት በበለፀገው መተግበሪያ የራዩ የ2016 ዓ/ም እጩ ተመራቂ ተማሪዎች ጥር 25/2016 ዓ/ም የሞዴል ፈተና ተሰጥቶ ነበር።
ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ትልቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱት የኢንጅነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ፣ ግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ፣ ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ፣ ተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ፣ የፈተናዎች ማስተባበርያ ማእከል እና የመረጃ፣ መገናኛ እና ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ከአቶ ሃፍቱ ኪሮስ እጅ የምስጋና ምስክር ወረቀት ተቀብለዋል።
በራዩ ከሶስት ዓመት በላይ በምክ/ፕረዚደንት እና የማኔጅመንት ካውንስል አባላት በመሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ ራዩ ምስጋናውን በማቅረብ የገንዘብ እና የራያ ባህል ልብስ ሽልማት እና የምስክር ወረቀት ከአቶ ሃፍቱ ኪሮስ ተሰጥተዋል።
በመጨረሻም አቶ ሃፍቱ ኪሮስ በመዝግያ ንግግራቸው ራዩ የተለያዩ ችግሮች ቢገጥሙትም ባለው ችግር ፈቺ የሰው ሀይል የበለፀጉ መተግበሪያዎች የተቋም ስብእና ለመገንባት፣ በውጤት የሚለካ አስተማማኝ ስራ ለመስራት፣ በሰው ሀይል እና ቴክኖሎጂ ለመደራጀት አስተዋፅኦ ያላቸው ፈጠራዎች ሊበረታቱ ይገባል ብለዋል።
******************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ሚያዝያ 05/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
ለበለጠ መረጃ