ራያ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር እና አሰባሰብ ስርዓት (HEIMS) ከፍተኛ ደረጃን ይዟል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ላለፉት ሶስት ዓመታት በክልሉ በነበረው ጦርነት ትልቅ የመረጃ እና መገናኛ ቴክኖሎጂ (ICT) መሰረተ ልማት ችግሮች ቢያጋጥሙትም ከጦርነቱ በኃላ ባደረገው እና እያደረገ ባለው ሁለንታዊ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር እና አሰባሰብ ስርዓት (HEIMS) 4ኛደረጃን ይዟል፡፡
ይህ ትልቅ ስኬት በመመዝገቡ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት በተለይም በመረጃ እና መገናኛ ቴክኖሎጂ (ICT) ዘርፍ ዩኒቨርሲቲው የላቀ ደረጃ ለመድረስ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡
የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና የከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር ስርዓት (HEIMS) ቡድን አባላት ባደረጉት ትጋት እና ቁርጠኛ ውሳኔ የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያለው የአካዳሚክ መረጃን ወደ ከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር ስርዓት (HEIMS) በተሳካ ሁኔታ በማስገባት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ የመረጃ ጥራት አያያዝን ለማሳደግ፣ አስፈላጊ መረጃዎችን ለማስገባት፣ በመረጃ ላይ የተመሰረቱ ውሳኔ ለመስጠት እና ጠንካራ የዲጂታላይዜሽን ስርዓት ለመፍጠር ወሳኝ ስራ ተሰርቷል፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር ስርዓት (HEIMS) ቡድን አባላት እንደገለፁት ራያ ዩኒቨርሲቲ ትክክለኛ እና ወቅታዊ የአካዳሚክ መረጃን ወደ በከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር ስርዓት (HEIMS) ፕላትፎርም ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲገባ ላደረገው ትጋት እና ጥረት ያለውን ምስጋና እና አድናቆት በመግለፅ በየከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር ስርዓት (HEIMS) ውስጥ የተከማቸ መረጃ አስተማማኝ እና እምነት የሚጣልበት መሆኑን ለማረጋገጥ ጠንክሮ መሰራት አለበት ብለዋል፡፡
ይህ ስኬት ዩኒቨርሲቲውን ከውስጥ ብቻ የሚጠቅም ሳይሆን ትክክለኛ እና ስትራተጂካዊ ውሳኔዎች፣ ዘገባዎችና ግንዛቤዎች ለውጭ ባለድርሻ አካላት የመስጠት አቅምን በማሳደግ የዩኒቨርሲቲውን የግልጽነት እና ተጠያቂነት ስርዓት ለመደገፍ የተደረገ ቁርጠኝነት ያሳያል።
******************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
መጋቢት 24/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አሥፈፃሚ
******************************
ለበለጠ መረጃ