በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን የተመራ ልኡክ ቡድን የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ ቁሳቁሶች በችግራችን ወቅት ለራያ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ ያበረከተ ብቸኛ ተቋም መሆኑን የሚታወስ ሲሆን ራያ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ ከተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በተለያየ ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው በመቐለ IDP Center ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና በርዕደ መሬት ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ የገቢ ረሱ ዞን አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳ ነዋሪዎች የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ድጋፉን ለመቐለ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ አቶ ጌቱ ሃይሉ እና የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ላቋቋመው የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረሃይል አስረክበዋል፡፡
በርክክቡ ወቅት የራያ እና የሰመራ ዩኒቨርሲቲዎች ፕረዚደንቶች፣ የገቢ ረሱ ዞን አመራሮች፣ የአደጋና ስጋት መከላከል ቢሮ አመራሮች፣ የተፈናቃዮቹ እና የማህበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።