የራያ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ በ2017 ዓ/ም የሠማእታት መታሰብያ አዳሪ ትምህርት ቤት እንዲቋቋም ወሰነ።

ከዩኒቨርሲቲው ተልእኮዎች መካከል የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት አንዱ መሆኑን ይታወቃል። ይህንን ተልእኮ እውን ለማድረግ በ8ኛ ክፍል እጅግ ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች እድል በመስጠት የነገ አገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር ዩኒቨርሲቲያችን የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት ያለመ ነው።
ይህንን ከግብ ለማድረስ ከየካቲት 01/2016 ዓ/ም ጀምሮ የአዳሪ ትምህርት ቤት ተቀዳሚ ዳይሬክተር መድቦ ሥራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ ይገኛል።
****************
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
👇👇👇