በዩኒቨርሲቲው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና አፈፃፀም መመርያ 919/2014 እና ዩኒቨርሲቲው በመውጫ ፈተናው ያደረገው ቅድመ ዝግጅት፣ ያጋጠሙት ችግሮች እና ቀሪ ስራዎች ትኩረት ያደረገ ውይይት ተካሄደ።

በዩኒቨርሲቲው የከፍተኛ ትምህርት አገራዊ ቅድመ ምረቃ የመውጫ ፈተናን በአግባቡ ለመምራትና ለማስተዳደር የተዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ማስፈፀሚያ መመሪያ የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና አፈፃፀም መመርያ 919/2014 እና ዩኒቨርሲቲው የ2016 ዓ/ም መውጫ ፈተና ዝግጅት፣ ያጋጠሙት ችግሮች እና ቀሪ ስራዎች ትኩረት ያደረገ ውይይት ዛሬ ግንቦት 25/2016 ዓ/ም ተካሄደ።
የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ሀገሪቱ የምትፈልገውን የሠለጠነ የሠው ሀይል ለማፍራት ራያ ዩኒቨርሲቲ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በውይይቱ የራያ ዩኒቨርሲቲ ፈተናዎች ማስተባበርያ ማእከል አስተባባሪ መ/ር ተስፋይ ሀረገወይን የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና አፈፃፀም መመርያ 919/2014 እና ማንዋል አስፈላጊነት፣ ዓላማ፣ ለመውጫ ፈተና ብቁ ስለመሆን፣ የምዝገባና ፈተና አሰጣጥ ስርዓት፣ ድጋሚ ስለመፈተን፣ የፈተናው ፋይዳ ተፅእኖ፣ አዎንታዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ተፈታኞች፣ የአስፈፃሚ አካላት ተግባርና ሀላፊነት፣ በፈተና አሰጣጥ ላይ የሚሳተፉ አካላት ስልጣን እና ተግባር፣ የዩኒቨርሲቲው የሎጂስቲክስ እና ቴክኒክ፣ የፈተና አስተዳደር፣ የፀጥታ እና ደህንንነት ግብረ ሀይል እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው ለመውጫ ፈተና ያደረገው ቅድመ ዝግጅት በዝርዝር ገለፃ አድርገዋል።
በውይይቱ የኮሌጅ ዲኖች፣ የ ICT ሰራተኞች፣ የኢትዮ ቴሌኮም ሰሜን ሪጅን ተወካዮች፣ የፀጥታ እና ደህንነት አካላት ተወካዮች፣ የኤሌክትሪክ ጥገና ባለሙያዎች እና ሌሎችጰየሚመለከታቸው አካላት የተሳተፉ ሲሆን ተሳታፊዎች ላነሷቸው የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች በዩኒቨርሲቲው የአካ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/አገ/ ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ነጋ ዓፈራ ምላሽ እና ማብራርያ ተሰጥቷል።
ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ባደረጉት የመዝግያ ንግግር መመሪያው በመውጫ ፈተና ዝግጅት ሊካተቱ ስለሚገባቸው ሃገራዊ ዝቅተኛ የትምህርት ብቃት መመዘኛዎችን፣ የሙያ ሥነ ምግባር ደምቦችን እና ተቋማት ሊከተሏቸው የሚገቡ የአሠራር ስነ- ስርዓቶችን ያካተተ ስለሆነ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች በየዘርፉ ውጤታማ ስራ መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።
*****************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ግንቦት 25/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*****************************
ለበለጠ መረጃ👇👇👇ይመልከቱ።