በዩኒቨርሲቲው ሲሰጥ የነበረው የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) በሰላም ተጠናቀቀ።

በራያ ዩኒቨርሲቲ ከሰኔ 14/2016 ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሰጠ የነበረው የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) ዛሬ ሰኔ 19/2016 ዓ/ም በሰላም ተጠናቀቀ።
በመውጫ ፈተናው ሊፈተኑ ከሚገባቸው 333 ተማሪዎች ወደ ፈተና የቀረቡት 325 ተማሪዎች ሲሆኑ የፈተና ሂደቱ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላደረጉ ሁሉም አካላት ዩኒቨርሲቲው ታላቅ ምስጋናውን ያቀርባል።
በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡ አስተባባሪዎች እና ፈታኝ መምህራን እንደገለፁት የመውጫ ፈተና ሂደቱ ሰላማዊ እና ፍትሃዊ ነበር ብለዋል።
መልካም እድል ለተማሪዎቻችን!
************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ሰኔ 19/2016 ዐዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!!!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አሥፈፃሚ
*************************************