(ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ህዳር 26/2018 ዓ/ም)
ህዳር 24 ቀን፣ 2018 ዓ/ም የተፈረመው ይህ ስምምነት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲቢኢ ብር ደመወዝ ከፋይ ለሆኑ መስሪያ ቤቶች ባመቻቸዉ የሲቢኢ ብር የዲጂታል ቁጠባና ብድር አገልግሎት የራያ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ከግማሽ ወር እስከ አራት ወር ደመወዝ የሚደርስ ብድር ያለምንም ዋስትና በተመጣጣኝ የአገልግሎት ክፍያ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው።
የመግባቢያ ስምምነቱን የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቐለ ዲስትሪክት ኃላፊ አቶ ኤልያስ ልሳነወርቅ የራያ ዩኒቨርሰሲቲ ከፈተኛ እና መካከለፃ አመራሮች እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቕለ ዲስትሪክት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ፈርመውታል።
የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ በፊርማ ስነ ስርዓቱ እንደተናገሩት፤ ራያ ዩኒቨርሲቲ በቀጣይ ለሚያከናውናቸው የመማር ማስተማር፣ የጥናትና ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎች እና ሌሎች ተግባራት ከፋይናንስ ተቋማት ጋር መስራት የሚጠበቅ በመሆኑ ይህንን ለማሳካት ዩኒቨርሲቲው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ማድረጉን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቐለ ዲስትሪክት ኃላፊ አቶ ኤልያስ ልሳነወርቅ በበኩላቸው ባንካቸው ማህበረሰቡን ለመጥቀም የተለያዩ የብድር አማራጮችን እያቀረበ መሆኑንና ከራያ ዩኒቨርሲቲ ጋር ያደረገው ስምምነትም የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ደህንነቱ በጠበቀ መልኩ በሲቢኢ በጄ በሚል መተግበሪያ ከ500 ብር እስከ 150,000 ብር ድረስ መበደር የሚያስችልና ባንኩ ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተለያዩ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ትልቅ መንገድ የሚከፍት መሆኑን ሃሳባቸውን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቐለ ዲስትሪክት የዲጂታል ባንኪንግ ስራ አስኪያጅ አቶ አማኑኤል ታደሰ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብድር ተደራሽነትን ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለማስፋት እየሠራቸው ካሉ ሥራዎች መካከል አንዱ የሆነው የሲቢኢ ብር ዲጂታል ቁጠባ እና ብድር አገልግሎት ለዩኒቨርሲቲው ሠራተኛው ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚሰጥና ዩኒቨርሲቲው ለሀገር የሚያበረክታቸው የእውቀትና የምርምር ስራ ለመደገፍ በጋራ እንደሚሰሩ አብራርተዋል።
==============================
እውቀት ለማህበረሰባዊ ለውጥ!
ራያ ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ

Users Last 7 days : 838
Users Last 30 days : 2580
Total Users : 26918