የራያ ዩኒቨርሲቲየሰው ሀይል አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ከግንቦት 14 እስከ 16/2013 ዓ/ም በመኾኒ ከተማ ሜዳ ራያ ሆቴል ባዘጋጀው የስልጠና መድረክ ለቤተ-መፃህፍትና ዶክሜንቴሽን ዳይሬክቶሬት ሰራተኞች የረቂቅ ክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ስልጠናው በንግግር የከፈቱት የአስተዳደር ልማት ምክትል ፕረዚደንት ልዩ ረዳት አቶ ትኩዬ ደርቤ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት በተለያዩ ስልጠናዎች ራሳችሁን ማብቃት ይጠበቅባቹሃል ብለዋል፡፡ ስልጠናው በዋናነት እራስን ማወቅ፣ ለራስህን የተስተካከለ ግምት መስጠት፣ የቡድን ስራ፣ የተግባቦት ክህሎት፣ የግጭት አፈታትና ግብ ማሳካት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር፡፡በዚህም ሰልጣኞቹ በስልጠናው ያገኙት የረቂቅ ክህሎት ከስራቸው በማዛመድ ለተገልጋዮች ውጤታማ አገልግሎት እንዲሰጡ ያግዘናል ብለዋል፡፡ ስልጠናው የሰጡት በዩኒቨርሲቲው የጋይዳንስና ካውንስሊንግ ዳይሬክቶሬት ባለመያዎች የሆኑት አቶ ገ/ሄር ወልዱና መ/ር ይርጋ ሃይሉ ናቸው፡፡